Você está na página 1de 10

Category 1

All About Multiple Sclerosis


      All About Multiple Sclerosis
         ትርጉም:  አቡበከር ቃሲም
        
             
                         

―Multiple Sclerosis(MS)  ምን ማለት ነው ?

        Multiple Sclerosis(MS)  ማለት በወጣት

ጎልማሶች ላይ የሚከሰት  የነርቭ የስራ ሂደት መዛባት

ነው።የ MS ምክንያት በግልፅ ባይታወቅም፤የጤና

ባለሙያዎች መልሱን ለማግኘት ብዙ እየጣሩ ነው።

ለ በሽታው ፍቱን መድሀኒት ባይገኝለትም የበሽታውን

ሂደት ለመቀነስ እና በሽታው ይበልጥ እንዳይስፋፋ

ህክምናዎች ይሰጥጣሉ።

   ― MS ተላላፊ በሽታ አይደለም፤እንዲሁም የ MS

ተጠቂዎችን ዕድሜ ርዝመት አያጠቃም። MS ን

ይበልጥ አዳጋች የሚያደርገው በበሽታው ከተያዙ

በኃላ ባለው ቆይታ ምክንያት ከበሽታው ጋር

የሚነሱትን ጥቃቶች እንደ MS ተጠቂ ያልሆኑ ሰዎች

በቀላሉ መመለስ አለመቻል ነው። በጊዜ መፍትሄ

ከተገኘለት ከጥቃቱ  ማገገም ይቻላል።

     ―Multiple Sclerosis(MS) በ central

nervous system (CNS) (የጭንቅላት እና የጀርባ

አጥንት ውህድ) ላይ የሚከሰት በሽታ ነው።ይህ

ህመም MYELIN የተባለውን የነርቭ ሽፋን ወይንም

AXONs የተባለውን የነርቭ ሽፋን ያጠቃል፤በሂደቱም

CNS  ውስጥ ላይ ያሉትን ነርቮችን ያጠቃል፤በዚህም

ምክንያት ከ Brain and Spinal cord የሚተላለፉ

መልእክቶች በአግባቡ አለመተላለፍን ያሰከትላል።


በዚህ ሰበብ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ስራቸውን

በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ መስራት ይቀንሳሉ ።

     ― የ MS ተጠቂዎች በበሽታው ምክንያት

የሚታየው ጉዳት እንደየተጠቂው ይለየያል።አንድ

አንድ  ተጠቂዎች ከበሽታው ለጥቂት አመታት

በመራቅ እስከወዲያኛው ከበሽታው ይርቃሉ፤ አንድ

አንድ ተጠቂዎች ደግሞ በበሽታው ይበለጥ

ይጠቃሉ።

     _አብዛኛውን የ MS ጥናት አድራጊዎች  MS   

     "autoimmune disease" ነው  የሚል እምነት

አላቸው። "autoimmune disease"ማለት በሽታ

ተከላካይ CNS ላይ ያሉትን የነርቭ አካልን እንደ በሽታ

ተህዋሲያን ሲያጠቃ ነው።በዚህ ሰበብ 'MYELIN'

የተባለው የነርቭ ሽፋን ይጎዳል።

      _ ይህ የሰውነት መጉረብረብ (inflammation)

ክልል "active lesions" ይባላል፤ይህ ጠባሳ ቦታ

'plaques' ይባላል። ይህ "plaques " በተባለው

ጠባሳ 'MYELIN' የተባለው የነርቭ ሽፋን

ይጎዳል።በዚህ "plaques" በተባለው  ጠባሳ

መጠን፣ቁጥር እና ተጠቂ ቦታ አማካኝነት የተለያዩ

ምልክቶች ይከሰታሉ።"Multiple Sclerosis"

የሚለው ቃል የመጣው 'Plaques' የተባለው ጠባሳ

ከታወቀ በኃላ ነው፤'Multiple' ማለት ብዙ ማለት

ሲሆን፤ 'sclerosis' ማለት ደግሞ ጠባሳ እንደማለት


ነው።

                       
                                  

  ― የ MS ን ምክንያት ለማወቅ በብዙ ጥናት

አድራዎች ጥናት ተደርጓል።አንድ አንድ አጥኚዎች

የበሽታው መንስኤ (measles, herpes, human

T-cell lymphoma, and Epstein-Barr) በተባሉ

ቫይረሶች መሆኑን ይገልፃሉ፤ አንድ አንድ አጥኚዎች

ደ ግሞ በሽታውን ከ vitamin D እጥረት ጋር

ያገናኛሉ።

            የበሽታው ተጠቂዎች: -

     ―MS በአሜሪካ ብቻ 350000 ሰዎችን

አጥቅቷል ፣አብዛኛው የ MS ተጠቂዎች  የመጀመሪያ

ምርመራቸውን የሚያውቁት  15~50 አመት

እድሜያቸው ነው።

  ― የ MS ስርጭት ሙሉ ለሙሉ በዘፈቀደ

አይደለም፣በአማካይ ሴቶች ከወንዶች 3 እጥፍ   

የመጠቃታቸው  እድል ከፍ ያለ ነው።በተጨማሪም

ይህ በሽታ ከ ቦታ መገኛ (latitude) ጋር

ይዛመዳል፣ከ   ምድር ወገብ በስተ ደቡብ እና በስተ

ሰሜን ራቅ ያሉ ነዋሪዎች በ MS የመጠቃታቸው

እድል በምድር ወገብ ቅርብ ከሆኑ ነዋሪዎች የበለጠ

ነው።

      ―MS ተላላፊ በሽታ ወይም በ ዘር የሚተላለፍ

ባይሆንም፣አንድ የቤተሰብ አባል ተጠቂ ከሆነ ሌላው


የ ቤተሰብ አባል የመጠቃቱ እድል የሰፋ

ነው።በአማካይ በ አሜሪካ ከ 1000 ሰዎች በአንዱ

ላይ  ይስተዋላል።

                          

      ―ሌላው ከበሽታው ሰበብ ጋር የሚገናኘው ሲጋራ

ማጨስ ነው።ሲጋራ የሚያጨሱ ሴቶች ሲጋራ

ከማያጨሱ ሴቶች 1.6 እጥፍ ያህል በ MS

የመጠቃቱ እድል ከፍ ያለ ነው።በተጨማሪም ሲጋራ

አጫሽ  የ MS ተጠቂዎች በሽታው የመሰፋፋት እድሉ

ከፍ ያለ ነው።

     የ MS ምልክቶች:-

–fatigue (ድካም)

–visual disorders ( የእይታ ችግር )

–numbness( መደንዘዝ )

–dizziness/vertigo ( መጥወልወል)

–bladder and bowel dysfunction (ሽንትን  

    መቆጣጠር አለመቻል )

–weakness ( መድከም )

–tremor

–impaired mobility (እንቅሰቃሴን አለመቻል)

–sexual dysfunction

–slurred speech ( መንተባተብ)

–spasticity (የሰውነት እንቅስቃሴን አለመቆጣጠር)

– leg stiffness (እግርን ለማንቀሳቀስ መቸገር)

–swallowing disorders (የጎረሱትን መዋጥ መቸገር)


–chronic aching pain (ስር የሰደደ ራስ ምታት)
–depression

–mild cognitive and memory difficulties ( የእርሳታ ችግር)

                            
         
      –MS የተለያየ ችግሮችን ቢያስተናግድም ሁሉም

የ MS  ተጠቂዎች አንድ አይነት ጥቃትን

አያስተናግዱም ።አንድ አንድ ተጠቂዎች አብዛኛውን

ጉዳት አንድ አንድ  ተጠቂዎች ደግሞ ከፊሉን

ያስተናግዳል። 

     ― አንድ የ MS ተጠቂ አንድ ወይም ከዚያ በላይ

ምልክቶችን ሲያይ ዶክተሩን/ሯን ማናገር አለበት/

ባት።በጥቂቱም ቢሆን አብዛኛውን የ MS

ምልክቶችን በህክምና መከላከል ይቻላል።በምግብ

እና በአካል ብቃት እነቅስቃሴ የተወሰኑ የ MS

ምልክቶችን ማስተካከል ይቻላል።ሁሉም የህክምና

ለውጥ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለውጥን በ

MS ጉዳይ ላይ ብቁ የሆኑ ዶክተሮችን ያማከረ

መሆን አለበት።

         ―ብዙ ጊዜ የ MS ምልክቶች ሀይለኛ በሆነ

   ድካም (Fatique) ውስጥ ይጠቃላሉ፤ በ ከሰዐቱ

ሰዐት በሽታው የመባስ፣አንዳንዴ ደግሞ የሰውነት

ሙቀት መጨመር ምልክቶቹ ይጨምራሉ።አብዛኞቹ

ምልክቶች በሙቀት መጠን መለዋወጥ ( አንዴ ከፍ

አንዴ ዝቅ ማለት)  በበሽታው ተጠቂዎች ላይ

ለውጦች ይስተዋላሉ።

         ― አንድ የ ቤተሰብ አባል የ MS ተጠቂ ከሆነ


የምክርን አገልግሎት ማግኘቱ ተጠቃሚ ያደርገዋል፣

የ በሽታው ተጠቂዎች በብዙ መልኩ አካላዊም ሆነ

ስሜታዊ  መጠቃትን ይጎዳሉ።ሙያዊ የሆነ የምክር

አገልግሎትን ማግኘት የተጠቂው ቤተሰብን ይረዳል።

                         

        

            ―ዋና ዋና የ MS አይነቶች: -

       1,በአማካይ  80% የሚሆኑት የ MS ተጠቂዎች

relapsing-remitting form of MS (RRMS)

( አንዴ ደህና መሆን ፣ አንዴ ማገርሸት)፤ይህ አይነቱ

MS ከሌሎቹ  የሚለየው  አንዳንድ ምልክቶች

ጊዜያዊ በሆነ መንገድ ማገርሸት በአበረዛኛው ከ 1

እስከ 3 ወር በመቆየት የሚያገረሽ(" relapses")

ሲሆን ተመለሶ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ

ከበሽታው የማገገም ("remission") ሁኔታ ነው።

       2, የ RRMS ተጠቂዎች ህክምናውን

ያልተከታተሉ እንደሆነ 90% የሚሆኑት ወደ

secondary progressive MS (SPMS)

ይሽጋገራሉ።እዚህ ደረጃ የሚደረሰው የ RRMS

ተጠቂው የ (relapses) ጊዜው ሲበዛ  እና

ሲደጋገም ነው።

                        

       3,80%  የሚሆነው የ MS ተጠቂ የመጀመሪያው

ደረጃ ላይ ሲሆን 20% የሚሆነው ተጠቂ ወደ

primary-progressive MS (PPMS)
ይሸጋገራል።ይህ ደረጃ እንደ RRMS  ፆታን ሳይለይ

በ እኩል ደረጃ ያጠቃል።

         4,ሌሎች የ MS አይነቶች ቢኖሩም እንደ ከዚህ

በፊቱ የተለመዱ አይደሉም፤ እንደ ምሳሌ ብናይ፤

benign፣progressive-relapsing MS (PRMS)

እና malignant or fulminant MS ፣የተባሉትን

መጥቀስ ይቻላል።

         የ MS ምርመራዎች:-

–Magnetic resonance imaging (MRI)

–Cerebrospinal fluid (CSF)


    
                        

     የ MS መድሀኒቶች: -

1,Betaseron

2,Avonex

3,Rebif

4,Copaxone

5,Novantrone

    * እንደ አጠቃላይ  ሀገራችን ኢትዮዺያ  ውስጥ

MS የማይታወቅ በመሆኑ፤ በቂ ህክምናውን ማግኘት

አልተቻለም፣የጠቀስናቸው መድሀኒቶችንም ሀገራችን

ኢትዮዺያ  ውስጥ ማግኘት አለመቻላችን፣ ሌላው

ቀርቶ የጠቀስናቸውን ምርመራዎችን በአግባቡ

አለማግኘታችን ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል።።


                            

 
    

        # ከ    All About Multiple Sclerosis


           Written by: Susan Wells Courtney
                               የተወሰደ

Você também pode gostar