Você está na página 1de 7

የኮምፒዩቲንግና የኤሌክትሪካል ምህንድስና ት/ቤት

በት/ቤቱ ለሚሠሩ ተጨማሪ ሥራዎች የሚሳተፉ


ባለሙያዎች ማወዳደሪያ

መመሪያ

የካቲት 2006 ዓ.ም


ይዘት

1. መግቢያ

2. የማወዳደሪያ መስፈርቶች

3. ተጨማሪ ድንጋጌዎች
1. መግቢያ
2. የማወዳደሪያ መስፈርቶች

1. ልምድ፡-

2.1 ከሥራው ጋር የተገናኘ ልምድ ፡ ማለት በሚወዳደርበት ሥራ ተያያዥነት ያለው የማሰልጠን


የሥራ /የተግባር ልምድ ያለው ማለት ነው፡፡ በዚህ ሥር ሁለት መስፈርቶች ተካተዋል፡-

ሀ/ተመሳሳይ ስልጠና የሰጠ፣

1. አንድ (1) እና ከዚያ በላይ የሰጠ 3%


2. ምንም ስልጠና ያልሰጠ 0%

ለ/ የሥራ /ተግባራዊ/ ከሥራው ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው ልምድ

3 የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ያቀረበ 12%


2 የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ያቀረበ 8%
1 የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ያቀረበ 4%
ምንም ያላቀረበ 0%
1.2 መደበኛ የሆነ የሥራ ልምድ
አሥር ዓመት እና ከዚያ በላይ ያገለገለ 15% የሚያገኝ ሆኖ ከዚያ በታች ላለ የሥራ ልምድ
በዚህ መነሻ ስሌት መሰረት ተሠርቶ ይያዛል/ ለምሳሌ - 3 ዓመት ከ6 ወር አገልግሎት
ያለው /3.5 የአገልግሎት ዘመን /1ዐ ዓመት/ 15% = 5.25% ያገኛል ማለት ነው

1.3 ከሥራው ጋር የተገናኘ የስልጠና ሰርተፊኬት


- ከታወቀ ተቋም ከሥራው ጋር አንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰርተፊኬት ካለው 5%ያገኛል::
- ከታወቀ ተቋም ከሥራው ጋር ተዛማጅነት ያለው አንድ ወይም ከዚያ በላይ ካለው 3%

2ኛ የትምህርት ደረጃ
2.1 ለረዳት ኘሮፌሰርና ከዚያ በላይ 25 %
2.2 ሌክቸረር 21%
2.3 ረዳት ሌክቸረር 15%
2.4 ረዳት ምሩቅ II 13%
2.5 ረዳት ምሩቅ I 11%
2.6 ቴክኒካል ረዳት 7%
3 “ Extra Curricula Activities”

- 5 እና ከዚያ በላይ ተሳትፎ ያለው 1ዐ%


- 4 ተሳትፎ ያለው 8%
- 3 ተሳትፎ ያለው 6%
- 2 ተሳትፎ ያለው 4%
- 1 ተሳትፎ ያለው 2%
- ምንም ተሳትፎ የሌለው 0%

4. ማህበረሰባዊ አገልግሎት
በማህረሰብ አገልግሎት 3 እና ከዚያ በላይ ተሳትፎ ያለው 7%
2 ጊዜ ተሰትፎ ያለው 5%
1 ጊዜ ተሳትፎ ያለው 3%
ምንም ተሳትፎ የሌለው 0%
5. የሥራ አፈፃፀም
በት/ቤቱ ጠቅላላ የሥራ አፈፃፀም የተገኘ ውጤት በሚከተለው መሰረት ይሆናል፡፡
[90 - 100) ያገኘ 10%
[85 - 90) // 9%
[8ዐ - 85) // 8%
[75 - 80) // 7%
[70 - 75) // 6%
[65 - 70) // 5%
[60 - 65) // 4%
ከ60 በታች አፈፃፀም ውጤት ያለው ምንም ነጥብ አይያዝለትም፡፡
6. የመነሻ ጹሁፍ / Concept Note)
ከፍተኛ ነጥብ 10% ሆኖ እንደመነሻ ጽሁፍ ጥንካሬ በቴክኒክ ኮሚቴው ተገምግሞ ነጥብ
የሚሰጠው ይሆናል፡፡
7. ፆታ
ለሴቶች ሙሉ 3% ይሰጣል፡፡
3. ተጨማሪ ድንጋጌዎች
3.1 ሥራ ስላመጣ ግለሰብ /ቡድን
አንድ ሥራ ወደ ት/ቤቱ በግለሰብ ወይም በቡድን ቢመጣ አምጭው አካል በቀጥታ
በስራው ይሳተፋል፡፡ ስራው በቡድን ከመጣ እያንዳንዱ የቡዱኑ አካል ስራው
ከመጣበት መስሪያ ቤት ስራው ወደ ት/ቤቱ እንዲመጣ ጥረት ማድረጉን የሚገልጽ
ደብዳቤ ማምጣት አለበት፡፡

ስራውን አምጪ ሰው ወይም ቡዱን በስራው መሳተፍ የማይችል ከሆነ ወይም


መስራት የማይፈልግ ከሆነ በቴክኒክ ኮሚቴ የሚወሰን ኮሚሽን ይታሰብለታል፡፡
ስራውን ለሚሠራው ቡድን አጋ» ( Facilitator) ሆኖ ሊመደብ ይችላል፡፡

3.2 በተዳጋጋሚ በአንድ ስራ ላይ ስለመሳተፍ


አንድ ሰው ከዚህ በፊት በአንድ ስራ ላይ ቢሳተፍ ሌላ ስራ ከመጣ ቅድሚያ
መስፈርቱን የሚያሟሉና ከዚህ በፊት ያልተሳተፉ እንዲሰሩት ይደረጋል፡፡
3.3 ስለተሰራ ሥራ
ተመሳሳይ ሥራ ሰርቻለሁ ያለ ቡድን ወይም ግለሰብ ቢመጣ እንደሌለው ሰው
ተወዳድሮ በስራው ይሳተፋል እንጅ በቀጥታ ስራው ሊሰጠው ወይም ምንም አይነት
እገዛ ሊደረግለት አይችልም፡፡
3.4 የስራ አፈፃፀም
ከዚህ በፊት ት/ቤቱ በመደበው ስራ ላይ ተሳትፎ የሚፈለገውን ውጤት ባያመጣ እንደ
ስራ አፈፃፀም ጉድለት ይታይበታል፡፡ የችግሩ መጠን ተገምግሞ ከጀመረው ስራ
እንዲወጣ ሊደረግ ይችላል፡፡ ከጥቅም ላይ ሊውል የማይችል ከስታንዳርድ በታች የሆነ
ሥራ ከተሰራ ከዚህ በኋላ በት/ቤቱ ስራ ላይ እንዳይሳተፍ ሊደረግ ይችላል፡፡
3.5 ከጫና በላይ ስራ በተመለከተ
በስራ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ መምህር ከጫና በላይ የማስተማር ስራ፣ ወይንም
የማስተዳደር ስራ ካለበት ተቀራራቢ ላመጣና ጫና ለሌለው ግለሰብ ወይም ቡድን
የሚሠጠው ሲሆን ውሳኔው ግን በቴክኒክ ኮሚቴ ተመርምሮ የሚወሰን ይሆናል፡፡
3.6 በነፃ ስለመሳተፍ
አንድ ስራ ላይ ያለምንም ክፍያ መሣተፍ የሚፈልግ ሰው ካለ ስራውን ከሚሠራው
ግለሰብ ወይም ቡድን ጋር ተወያይቶ ከተፈቀደለት መግባት ይችላል፡፡ በስራው ላይ
መሳተፉን የቴክኒክ ኮሚቴ አጣርቶ የልምድ ሰርተፊኬት ሊሠጠው ይችላል፡፡
3.7 የዲስኘሊን ጉዳይ
አንድ መምህር የዲስኘሊን ችግር ሲኖርበት እርሱ ሊሳተፍ የሚችለውን ተካታተይ
ሁለት ስራዎች እንዲያልፉት ይደረጋል፡፡

Você também pode gostar