Você está na página 1de 44

በዴንቨር ኮሎራዶ

የኢትዮዽያ ወንጌላዊት
ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀ
ኤፕኤፕddሪ

አርዕስታዊ ተከታታይ
የመጽሐፍ ቅዱስ
ጥናት
/Topical Bible Study Series/

EECD Denver ,CO April 2017


አርዕስት ማውጫ ገፅ
መግቢያ ...............................................................................................................................................................3
ክፍል አንድ: ሰባቱ የኢየሱስ እኔ ነኞች ............................................................................................ 4

ጥናት 1.1የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ ................................................................................................................ 5


ጥናት1. 2 እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ..................................................................................................................... 6

ጥናት1. 3 የበጎች በር እኔ ነኝ ............................................................................................................................. 7


ጥናት1.4 መልካም እረኛ እኔ ነኝ ........................................................................................................................ 8

ጥናት1.5 ትንሳኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ .............................................................................................................. 9

ጥናት1.6 እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ ...............................................................................................................10


ጥናት1.7 እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ .........................................................................................................................11
ክፍል ሁለት: ከኢየሱስ ተዓምራቶች ውስጥ ሰባቱ ..................................................................... 12

ጥናት 2.1 የምልክቶች መጀመሪያ /የኢየሱስ ስልጣን በዓይነት ላይ/Miracle of Quality/ ............................... 13

ጥናት 2.2 የሹሙ ልጅ ፈውስ /የኢየሱስ ስልጣን በርቀት ላይ /Authority of Jesus over Distance/ ............... 14

ጥናት 2.3 የቤተ ሳይዳው ፈውስ/የኢየሱስ ስልጣን በጊዜ ላይ/Authority of Jesus over Time/ ....................... 15

ጥናት 2.4 አምስት ሺ ህዝብ መመገቡ/የኢየሱስ ስልጣን በመጠን ላይ/ Miracle of Quantity/ ........................ 16

ጥናት 2.5 በውኃ ላይ መራመዱ/የኢየሱስ ስልጣን በተፈጥሮ ላይ/Authority of Jesus over Nature/ ............. 17

ጥናት 2.6 ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደው ሰው ፈውስ/ የኢየሱስ ስልጣን በማንኛውም ድውይ ላይ /Authority of
Jesus over any Illness/ .............................................................................................................................. 18

ጥናት 2.7 የአልዓዛር ከሞት መነሳት /የኢየሱስ ስልጣን በሞት ላይ/Authority of Jesus over Death/ ............ 19
ክፍል ሦስት: ወደ ኢየሱስ ከቀረቡ ሰዎች መካከል ሰባቱ .......................................................... 20

ጥናት 3.1 በአጋንንት የተያዘው ሰው ..............................................................................................................................21


ጥናት 3.2 ለአስራ ሁለት ዓመታት ደም ይፈሳት የነበረች ሴት ........................................................................... 22

ጥናት 3.3 ኢየሱስን ሽቱ የቀባች ኃጢአተኛ ሴት .............................................................................................................23


ጥናት 3.4 ቀረጥ ሰብሳቢው ዘኬዎስ ................................................................................................................ 24

ጥናት 3.5 የሕግ መምህሩ ኒቆዲሞስ ................................................................................................................................25


ጥናት 3.6 ሳምራዊቷ ሴት .............................................................................................................................. 26
ጥናት 3.7 በምንዝር የተያዘች ሴት .......................................................................................................... 2
አርዕስት ማውጫ ገፅ

ክፍል አራት: ተጣራሽ/ Paradoxic)/ከሚመስሉ አስተምህሮቶች ሰባቱ ....................................... 28

ጥናት 4.1 በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አለመጨነቅ .................................................................................... 29

ጥናት 4.2 ራስን በመካድ ነፍስን ማዳን ............................................................................................ 30

ጥናት 4.3 ሞኝነት የሚመስል ጥበብ ................................................................................................. 31

ጥናት 4.4 ደካማን ኃያል ሰው የሚያደርግ ጸጋ ................................................................................... 32

ጥናት 4.5 ትህትና የከፍታ ሚስጥር ................................................................................................. 33

ጥናት 4.6 ረብ የሆነውን በመጣል ወደ ፊት ........................................................................................ 34

ጥናት 4. 7 በሁካታ ውስጥ የማነጥፍ ደስታ ...................................................................................... 35

ክፍል አምስት: ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ................................................................................... 36

ጥናት 5.1 ኤፌሶን ........................................................................................................................... 37

ጥናት 5.2 ሰምርኔስ .......................................................................................................................................... 38


ጥናት 5.3 ጴርጋሞን ......................................................................................................................................... 39
ጥናት 5.4 ትያጥሮን ....................................................................................................................... 40
ጥናት 5.5 ሰርዴስ ............................................................................................................................ 41

ጥናት 5.6 ፊላድልፍያ ....................................................................................................................................... 42


ጥናት 5.7 ሎዶቅያ ............................................................................................................................................ 43
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

መግቢያ

ካሁን ቀደም በተለይም ባለፉት ሦስት ወይም አራት ተካታታይ ዓመታት በቤተ ክርስቲያናችን ያደረግናቸው
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት ውጥስ የተወሰኑትን በመምረጥ መሉውን መጽሐፍ
በተከታታይ አጥንተን ማጠናቀቃችን ይታወሳል። ለምሳሌ ለማስታወስ ያህል የሉቃስ ወንጌልንና የሐዋርያትን ስራ
መጽሐፍቶች መጥቀስ ይቻላል።በዚህ ሁሉ ጌታ ስለረዳንና ጸጋውን ስላበዛልን ክብር ሁሉ ተጠቅልሎ ለእርሱ ብቻ
ይሁን። በጥናቶቹ በትጋትና በንቃት ያለማቁዋረጥ የተሳተፋቹትን ሁሉ ጌታ አብዝቶ ይባርካቹ አሁንም ጸጋውን
ያብዛላችሁ ልንል እንወዳለን።

የአቀራረብ ዘዴ/Method/: የዚህኛው ዙር ጥናት አቀራረብ እንደ አሁን ቀደሙ አንድ ወጥ መጽሐፍ/Book/
አጥንቶ ማጠናቀቅ ሳይሆን እንዲጠኑ በመረጥናቸው የተለያዩ አርዕስቶች/Topics/ ከተለያዩ መጽሐፍቶች የተወሰኑ
ክፍሎችን/Chapters/በመውሰድ ነው። የአጠናን ዘዴአችን ደግሞ በዛው ከዚህ ቀደም በምናደርገው አጠናን ዘዴ
ማለትም /Inductive Method of Bible Study/ መሠረት ማድረግ ይሆናል። እነዚህ ተከታታይ ጥናቶች ምንም
እንኳን የተለይታዩ ቢሆኑም ሙሉ በሙሉ ከራዕይ መጽሐፍ ከተወሰዱ ሰባት ጥናቶች ብቻ በስጠቀር አብዛኞቹ
ከአዲስ ኪዳን በተለይም ከወንጌላት: ከወንጌላትም ውስጥ በብዛት ሐዋርያው ዮሐንስ የዘገባቸውን ሲሆን
ከደብዳቤዎች ደግሞ አብዛኞቹ ከሐዋርያው ጳውሎስ መልዕክቶች ውስጥ የተወሰዱ ነው ማለት ይቻላል።

የጥናቱ ሽፋን/ Scope/: ይህ ጥናት አምስት የተለያዩ ዐብይ ክፍሎች ሲኖሩት እያንዳንዱ ክፍል ላይ ደግሞ ሰባት
ተከታታይ ንዑሳን አርዕስቶች በድምሩ ሠላሳ አምስት ጥናቶች ተዋቅረውበታል። አምስቱ ዋና ዋና ክፍሎች
የሚከተሉት ናቸው: ሰባቱ የኢየሱስ እኔ ነኞች፣ ከኢየሱስ ተዓምራቶች ውጥስ ሰባቱ፣ ኢየሱስ ጋ ከቀረቡ ሰዎች ውጥስ
ሰባቱ፣ ተጣራሽ /ፓራዶክሲክ/ ከሚመስሉ ትምህሮቶች ውስጥ ሰባቱ እና ስለ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።

ዓላማ/Objective/: የዚህኛው ዙር ጥናት ዋነኛ ዓላማ ታውቆ ስለማያልቀው ስለ ክርስቶስ ማንነት የበለጠ
እንድናውቅ እንዲረዳን፣ኢየሱስ ጋ ቀርበው በእርሱ ስለተጎበኙ በርካታ ሰዎች ጥቂቶቹን እንደ ምሳሌ ለማቅረብ ፣
ለእኛም ለትምህርታችን ስለተጻፉልን መልክቶችና ለቤተ ክርስቲያንም ስለተሰጠ ተስፋና ማስጠንቀቂያ ለመዳሳስና
ከዚያም በግላችን፣ በአገልግሎት ቡድኖቻችንና በቤተ ክርስቲያናችን ለመጸለይና የተማርነውንም በሕይወት
በመተግበር ለውጥ ማሳየት እንድንጀምር እንዲረዳን ነው።

ማሳሰብያ/ Remarks/: በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‘7 ‘ቁጥር እንደ መለኮታዊ ፍጻሜ ፣የእረፍት፣የድልና
የመታሰቢያ /Divine completeness,Perfection, and Wholeness /ዘፍ 2:3 ዘጸ16:29 ፣ኢያ 6:15/ ማሳያ
ተደርጎ ሲወሰድ ይታያል።ለምሳሌ በዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ብቻ ከሃምሳ ጊዜ በላይ ባጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ ደግሞ ከሰባት መቶ ጊዜ በላይ ያህል ‘7 ‘ቁጥር በተለያዩ የትርጉም ዐውዶች አገልግሎት ላይ ውሏል።ስለዚህ
እኛም ሰባትን የመረጥንበት ምክንያት ከዚህ እምነትና መልካም ምኞት በመነጨና ለጥናት አያያዝም ስለሚያመች
እንደዚሁም ከዚህ በላይ ለማቅረብ ከጊዜአችን የተነሳ ለአሁኑ ጥናታችን በሰባት ለመወሰን ስለተገደድን ጥቂቶቹን
ብቻ አንስቶ ለመነጋገር እንጂ ጥናቱ ላይ የተካተቱት አንዳንዶቹ በትክክልም ሰባት ጊዜ ብቻ የተፈጸሙ ሁኔታዎችን
አመልካች ቢሆኑም በዚህ ጥናት ላይ የተጠቀሱት ሁሉም ግን ሰባቱ ብቻ ናቸው ማለታችን በፍጹም አይደለም።

ጌታ የተባረከ ጊዜ ይስጠን።አሜን!

3
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ክፍል አንድ: ሰባቱ የኢየሱስ እኔ ነኞች

መግቢያ፡- በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር አብ በተለያዩ ሁኔታዎች “እኔ ነኝ” በማለት ማስተማሩን እናውቃለን፡፡ አንድ
ለመጥቀስ ያህል ሙሴ ማን እንደላከው ሲናገር “እኔ ነኝ” የሚለውን የጌትነት እና ዘላለማዊነት ስሙን ነግሮታል፡፡
ጌታችንም ይህንን ስሙን በምድር በነበረበት ጊዜ ደጋግም አስተምሮአል፡፡

1. በብሉይ ኪዳን መና የተሰጣቸው ሲሆን (ዘጸ 16፡4፣15) እርሱ ራሱ የህይወት እንጀራ መሆኑን ፡፡ (ዮሐ 6፡35)
2. በዘጸ 13፡21 በደመናና በእሳት ሲመሩ እርሱ ግን ራሱ የዓለም ብርሃን መሆኑን (ዮሐ 8፡22) ፡፡
3. በዮሐ 10፡7 እርሱ የበጎች በር እና ከለላ እንደሆነልን ፡፡
4. በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር እረኝነት (መዝ 23፡1 ፣ ኢሳ 40፡11) የተገለጸ ሲሆን ኢየሱስ ደግም ራሱ እረኛ
(ዮሐ 10፡11፣ 14) መሆኑን፡፡
5. በዳን 12፡2 ስለሙታን ትንሣኤ የተነገረ መልዕክት ሲኖር እርሱ ግን እራሱ ትንሣኤ እና ሕይወት መሆኑን
አስተምሮናል፡፡ (ዮሐ 11፡25)
6. በብሉይ ኪዳን ህግ የተሰጠ ሲሆን አሁን ደግሞ ራሱ ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምንደርስበት መንገድ
እውነትና ህይወት ሆኖልን (ዮሐ 14፡6) መገለጡን ፡፡
7. በኢሳ 5፡ 1–7 እስራኤል በወይን የተመሰለ የእግዚአብሔር ህዝብ ሲሆን በዮሐ 15፣1 ኢየሱስ እውነተኛ
የወይን ግንድ መሆኑን ይነግረናል ፡፡

በመሆኑም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ስጋን ለብሶ መጥቶ ለእኛ አማኑኤል መሆኑንና በእርሱ
ለሚያምኑት የማዳን ብቃት ያለው መሆኑን “እኔ ነኝ” በማለት ካስተማረው ትምህርቶች በሚጥሉት አርዕስቶች
በሚቀርቡት ሰባት ተከታታይ ጥናቶች እንደሚከተሉት እንመለከታለን፡፡

ጥናት 1.1“የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ “


ጥናት1. 2 “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ”

ጥናት1.3 “የበጎች በር እኔ ነኝ”


ጥናት1.4 “መልካም እረኛ እኔ ነኝ”

ጥናት 1.5 “ትንሳኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ”

ጥናት1.6 “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ”

ጥናት 1.7” እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ” የሚሉት ናቸው፡፡

4
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት1.1: “የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ”

የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ 6፡ 25 – 51

መግቢያ፡- የክፍል አንድ መጀመሪያ በሆነው በዛሬው ጥናታችን ኢየሱስ “የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ” ወደ እኔም
የሚመጣ ከቶ አይራብም ብሎ ለብዙ ሕዝብ እንዳስተማረ እናያለን ፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ኢየሱስ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለበላችሁና ስለ ጠገባችሁ እንጂ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም ሲልምን
ማለቱ ነው?
2. የእግዚአብሔር ስራ እንድንሰራ ምን እናድርግ ብለው ሲጠይቁት ምን መልስ ሰጣቸው? ምላሻቸውን አይቶ
ኢየሱስ የሰጠውን መልስ አብራራ፡፡ (ዮሐ 6፡28 – 33)
3. ኢየሱስ የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም ሲል ምን ማለቱ ነው? የላከኝ የአብ
ፈቃድ ይህ ነው ያለውስ ምንድን ነው?
4. አይሁድ እያንጎራጎሩ አባቱንና እናቱን የምናውቃቸው የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? ያሉበት ምክንያት
ምንድን ነው? ኢየሱስስ ምን መልስ ሰጠ?
5. አብን ያየ ማንም የለም ከእግዚአብሔር ከሆነው በቀር እርሱ አብን አይቶአል ማለቱ ምን ለማስዳት
ይመስልሃል/ሻል?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. ኢየሱስ “የላከኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው እንዳለ ሁሉ አኛም ይህ የእግዚአብሔር በጎ ፍቃድ ነው ለማለት


የምንደፍርበት ምክንያቶች ምን መሆን ይገባዋል?
7. ጌታን ለመከተል ውሳኔ ያደረግነው ከምን የተነሳ እንደሆነ ተሞክሮህን ለቡድንህ አካፍል?

ማጠቃለያ

በዚህ ምድር የምናያቸውና የምንጓጓላቸው ነገሮች ሁሉ አንዳቸውም ለህይወታችን ዘላለማዊ ዋስትና ሊሰጡ
አይችሉም፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ግን ለዘላለም የህይወት እንጀራ ነው፡፡ ማንም ከእርሱ በልቶ
ለዘላለም አይራብም ከልጁ መታዘዝ የተነሳ ምህረቱና ቸርነቱ የሰው ልጆች አምነው እንዲቀበሉት ተሰጥቶናል ይህንን
ታላቅ ጸጋ ለሰዎች ሁሉ በመጋበዝ የታረዘችን ነፍስ በህይወት እናትርፍ፡፡

በቃል የሚጠና

“የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም “ዮሐ 6፡35

5
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት1. 2: “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ”

የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ 8፡ 12 – 30

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ኢየሱስ “የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ “ወደ እኔም የሚመጣ ከቶ አይራብም ብሎ ለብዙ
ሕዝብ እንዳስተማረ ተመልክተን ነበር ፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ብርሃን ስለመሆኑና
እርሱን የሚከተል ሁሉ በብርሃን እንደሚመላለስ የተናገረውን እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ፈሪሳውያን ኢየሱስን ስለስራህ የምትናገረው ምስክርነት እውነት አይደለም ያሉት ምን ስለተናገራቸው


ነበር? የተናገረውንስ ሀሳብ ስለምን መቀበል አቃታቸው?
2. ኢየሱስ ለፈሪሳውያን በሰጠው መልስ “የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ነው እንጂ ብቻዬን አይደለሁም እንዲሁም
የላከኝ አብ ስለእኔ ይመሰከራል” ሊል ምን ማለቱ ነው?
3. ፈሪሳውያንን ኢየሱስ እኔንም ወይም አባቴን አታውቁም ብሎ የተናገራቸው ከምን የተነሳ ነው?
4. እኔ እሄዳለሁ ትፈልጉኝማላችሁ በሀጢያታችሁ ትሞታላችሁ ሲል የአይሁድ መረዳት ምን ነበር? ኢየሱስ
ምን እየተናገራቸው ነበር?
5. ብዙዎች በእርሱ እንዲያምኑ ያደረጋቸው የኢየሱስ ክርስቶስ ንግግር ምንድን ነበር? ምንስ ትምህርት
ያስጨበጣቸው ይመስልሃል/ሻል?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. በምንኖርበት ህብረተሰብ ውስጥ የህይወት ብርሃን መሆን የምንችለው እንዴት ነው?


7. ክርስቶስ “አንተ ማነህ” ተብሎ በማያምኑት ሰዎች አንደተጠየቀ ዛሬም ስለ እርሱ ማንነት በማያምኑ ሰዎች
ብንጠየቅ እንዴት ልንገልፀው እንደሚገባን ተወያዩበት፡፡

ማጠቃለያ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብ እንደላከውና እርሱም የአለም ብርሃን እንደሆነ ሲነገር ምስክርነቱን
ሊቀበሉ ያልወደዱ አንተ ማነህ? እስከማለት ቢጠይቁም እርሱ በነቢያት የተነገረው ክርስቶስ እንደሆነ እየተነገረ
ብዙዎች በእርሱ እንዲያምኑ አደረገ የእኛም ሀላፊነት ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የጠራንን ጌታ እየገለጽን
ሰዎችን ወደ ዘላለማዊ ህይወት እንዲመጡ ማስተዋወቅ ነው፡፡

በቃል የሚጠና

“እኔ የአለም ብርሃን ነኝ” ዮሐ 8፡12

6
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት1.3” የበጎች በር እኔ ነኝ”


የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ 10፡ 1 – 10

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ብርሃን ስለመሆኑና እርሱን የሚከተል ሁሉ በብርሃን
እንደሚመላለስ የተናገረውን ተመልክተን ነበር ፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ እርሱ ራሱ የበጎች በር ስለመሆኑ
በምሳሌ ያስተማረበትን ክፍል እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በዚህ ክፍል ከቁ 1–3 ላይ የተዘረዘሩት ምን እና ምን ሃሳቦች ናቸው? ከዚህስ ምንባብ ምን እንረዳለን?


2. በቁ. 4 ላይ ስንመለከት በጎቼን በምን ዓይነት መንገድ ነው የሚመራቸው? ስለምንስ ከኋላ ያልነዳቸው
ይመስላችኋል?
3. ከቁ. 7 – 8 ስንመለከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ራሱ ምን ብሎ ይመሰክራል?
4. በቁ. 9 ላይ ኢየሱስ “በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፣ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል” ሲል ምን
ማለቱ ነው? የሚድነውስ ከምንድር ነው?
5. በቁ. 10 ላይ ስለተጠቀሰው (…ሌባው…) ምን ታስተውላለህ/ለሽ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለው ልዩነት
ምን ትላለህ/ሽ?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. ዛሬስ እኛ ኢየሱስ ክርስቶስን በስማችን እነሚጠራን አውቀን ድምጹን ከቃሉና ከመንፈሱ ሰምተን በየዕለቱ
በሕይወታችን በትክክል እንከተለዋለን?
7. ለሌሎችስ የንፍስ መዳን መግቢያው በር ኢየሱስ እርሱ ብቻ መሆኑን ምን ያህል እንነግራቸዋለን?

ማጠቃለያ

ምንም እንኳ እኛ ባለንበት በዚህ የመጨረሻ ዘመን እጅግ የበዙ አሳሳች ድምጾችና ሰፋፊ የጥፋት በሮች የተከፈቱ
ቢሆንም የነፍሳችን መዳኛ እውነተኛ በር ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑን በመረዳት ሁል ጊዜ ከቃሉ ድምጹን
በመስማት ሕይወታችንን ልንመራና ለሌሎችም ይሕንን ብቸኛ የመዳን መግቢያ በር ልናሳያቸው ይጠበቅብናል።

በቃል የሚጠና

“ኢየሱስም ደግሞ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ እኔ የበጎች በር ነኝ። ” ዮሐ10፡ 7

7
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት1.4: “መልካም እረኛ እኔ ነኝ”

የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ10፡ 11 – 18

መግቢያ፡-ባለፈው ጥናት ኢየሱስ ክርስቶስ የበጎች በር ስለመሆኑ በምሳሌ ያስተማረበትን ክፍል ተመልክተን ነበር፡፡
በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ራሱ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ” ብሎ ካስተማረው እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ኢየሱስ በቁ. 11 ና 14 ላይ መልካም እረኛ እንደሆነ ይናገራል የመልካም እረኛ ባህሪያት ለቁ. 11 – 15
ባለው ላይ የተገለፀውን እንዲሁም መልካም ስላልሆነው እረኛ የተገለፀውን ባህሪያት ተወያዩበት፡፡
ከመዝሙር 22፡ 1 – 6 በተለይም ቁ.1ን ተመልከቱ:
2. በቁ. 16 ላይ ኢየሱስ “ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ” ሲል እነ ማንን ማለቱ ይመስልሃል /ሻል?
የበጎቹስ ባሕርይ ምን ዓይነት ነው?
3. ኢየሱስ በጎቹን ወደ በረቱ የሚያመጣቸው በምን ዓይነት መንገድ ነው?
4. ኢየሱስ አብ ይወደኛል ያለው በምን ምክንያት ነው?
5. በቁ. 18 ላይ እኔ በፈቃዴ አኖራታለው እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም ሲል ስለ መታዘዙ እና
ስለፍቅሩ ምን ትረዳለህ?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. እኛ ሁላችን ደግሞ የወንድሞቻችን እና የእህቶቻችን ጠባቂዎች እንደሆንን በአቤል እና በቃየል ታሪክ


በዘፍ 9:4 ላይ እናያለን፡፡ እንግዲህ ምን ዓይነት እረኞች ነን? ክፉው እንዳያገኛቸው ለወንድሞቻችን እና
ለእህቶቻችን እንጠነቀቃለን? ሕይወታችንን እስከመቁረስ ድረስ ለሌሎች እንጠነቀቃለን? ወይንስ
ኑሮአችን እንደመልካም እረኛ ሳይሆን እንደባለሙያው በራሳችን ዙሪያ የሚያጠነጥን ነውን?

ማጠቃለያ

የልጁን መልክ እንድንመስል አስቀድሞ የወሰነን እና የጠራንን አምላክ ልናከብር፤ ጌታችን እና መድሀኒታችን መርቆ
በሰጠን አዲስ እና ህያው የሆነ መንገድ (ሕይወት) ልናከብረው፤ የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው እና የእረኞች አለቃ
ከመገለጡ በፊት እንደ መልካም እረኛ እና ደጋግ መጋቢዎች ጌታ ልናገለግለው ጠርቶናል እና በጌታ ላይ ተደግፈን
በፊታችን ያለውን ሩጫ በትጋት ለመፈጸም እንትጋ፡፡

በቃል የሚጠና

” መልካም እረኛ እኔ ነኝ መልካም እረኛ ነፍሱን ስለበጎቹ ስለበጎቼ ያኖራል፡፡” ዮሐ 10፡11

8
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 1.5: “ትንሳኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ”

የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ11፡ 1 – 27

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ” ብሎ ካስተማረው የመልካሙን እረኛ
ባሕርይ እና ፍቃድ እንዲሁም መልካም ያልሆነው (ክፉው) እረኛ ባህሪያትን በዝርዝር ተመልክተን ነበር። በዛሬው
ጥናታችን ደግሞ ኢየሱስ “ትንሳኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ “ብሎ ያስተማረውን ትምህርት እንዲሁም ለማርታና
ለማርያም ያደረገውን እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ከቁ.1– 3 ባለው ክፍል ስለማን ታሪክ ተጽፏል? በዚህ ክፍል የተፈጠረው ነገር ምን ነበር? ምንስ እርምጃ
ተወሰደ?
2. ኢየሱስ የሰጠው ምላሽ ምን ይመስል ነበር? ስለ እነዚህስ ቤተሰብ የነበረው አመለካከት ምን ይመስላል?
ምንስ ውሳኔ ወሰነ? ከችግሩ አኳያ ሲታይ የወሰነው ውሳኔ ለቤተሰቡ ቢታወቅ ምን ሊሉ እንደሚችሉ
ትገምታለህ/ቻለሽ?
3. በቁ.7 ላይ እንደምንመለከታው ጌታ ለደቀመዛሙርቱ ወደ ይሁዳ እንሂድ ሲላቸው ምን አሉ? ለምንስ
እንደዛ ሊሉ የቻሉ ይመስልሃል ከምዕራፍ 10: 31 ጋር በማመላከት ተወያዩበት፡፡
4. ጌታ በቁ. 15 ላይ ስለ አልዓዛር መሞት በግልጥ ከነገራቸው በኋላ ቶማስ ለባልንጀሮቹ ምን ብሎ ተናገረ?
ይህንስ ያለበት ምክንያት ለምን ነበር?
5. ማርታ ኢየሱስ እንደመጣ በሰማች ጊዜ ምን አገረገች? ምንስ አለች?
6. ኢየሱስ ምን አለ? ማርታስ በእግዚአብሔር ቃል እውቀተዋ ላይ በመደገፍ የተናገረችው ምን ነበር? ጌታስ
ይናገር የነበረው ሚስጥር ምን እንደነበር ተወያዩበት፡፡

ከህይወት ማዛመድ

7. በመጀመሪያ ደረጃ የሚያምኑብኝ ሁሉ ሕያዋን ናቸው ብሎ ሲናገር በእርሱ ያሉ ሕያዋን መሆናቸውን


እንዲሁም ደግሞ ከሞት ወዲህ ቢሆን በኋላ በህይወት እንደሚኖሩ አስተዋልክ/ሽን?
8. ጌታ ትንሳኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ ሲል ለሞተ ነገር ሁሉ ሕይወት መስጠት የሚችል አምላክ መሆኑን
ተረዳህን/ሽን?

ማጠቃለያ

በእርሱ የሚያምን ሁሉ ከሞት ወደ ህይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ ከቶ አይመጣም እንደሚል ጌታ በመንፈሱ
ለሚሞተው ሰውነታችን ባመንን ጊዜ ህይወት ሰጠው፡፡ በመኖራችን ደግሞ የእርሱን ህያውነት በሰውነታችን
ተሸክመን እንኖራለን፡፡ ለጌታ የሚሳነው ነገር የለምና ተስፋ በቆረጥንበት ብርታት አለቀበት፤ አበቃለት ባልነው ነገር
እንኳን ሕይወት ሰጥቶ ያራምደናል፡፡ በእርሱ ልንታመን፣ ልንደገፍና በእምነት ወደፊት ልንራመድ ይገባናል፡፡

በቃል የሚጠና

” ኢየሱስም፡-ትንሳኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳን ሕያው ይሆናል፡፡” ዮሐ11፡25

9
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት1.6: “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ”

የምንባብ ክፍል፡-ዮሐ 14፡1–16

መግቢያ፡ ባለፈው ጥናት ጌታችን -ኢየሱስ “ትንሳኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ “ብሎ ያስተማረውን ትምህርት እንዲሁም
ለማርታና ለማርያም ያደረገውን ተመልክተን ነበር። በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ኢየሱስ በምድራዊ ህይወቱ መጨረሻ
ሊደርስበት ያለውን ለሐዋሪያቶቹ ከተናገረና አብሮአቸው ከበላ በኋላ ሊመጣ ያለው ነገር እንዳያውካቸውና
ማንነቱንና አብሮነቱን “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ” ብሎ ሲያስረዳቸው እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በክፍሉ ውስጥ ኢየሱስ የተናገረውን ለእነማን ነው? ሊያውካቸውስ የሚያስችል ምን ሁኔታ ነበር?
እርሱንስ?
2. “በእግዚአብሔር እመኑ በእኔ ደግም እመኑ” ሲል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስና ስለ እግዚአብሔር አብ አንድነት
ምን ያሳያል? በዮሐ 12፡44 – 46 ካለው ክፍል ጋር አስተያይተህ መልስ፡፡
3. ቶማስ መንገዱን (ወልድ ወደሚሄድበት) ለማወቅ ለጠየቀው ጥያቄ የሰጠው መልስ ስለ ማንነቱና ስለ
ጌትነቱ ምን ያስረዳል? ይሄስ ከሌሎች የሃይማኖት መሪዎች ምን ልዩነት አለው?
4. በቁ 3 ላይ እና በ 1ኛ ተሰ 4፡ 16 – 17 ባለበት መጥቶ እንደሚወስዳቸው የነገራቸው መልዕክት ምን ያህል
ተስፋ ይሰጣቸዋል?
5. ፊሊጶስ አብን ማየት ለአሁኑ ችግር መፍትሄ በቂ መልስ ነው ሲል ጌታስ ስለ እርሱና ስለ አብ
ያስተማራቸውን አብራራ (ቁ 7 –11)
6. ጌታ ተመልሶ እስኪወስዳቸው ድረስ በምን ዓይነት ሁኔታ አብሮአቸው እንደምሆን አስተማራቸው? ይሄስ
ለፊልጶስ ጥያቄ በቂ መጽናናት ያመጣል ብለህ ታስባለህ? (ቁ12 –16)

ከህይወት ጋር ማዛመድ

7. በኢየሱስ ማመንና ጌትነቱን ማወቅ ለዛሬው ኑሮህ በቂ መፍትሄ ሆኖልሃል? ምን ለውጥ በሕይወትህ
ማድረግ ይኖርብሃል?

ማጠቃለያ

ጌታችን ኢየሱስ ዛሬ በአካል ከእኛ ጋር ባይሆንም ከፈጸመው ስራ የተነሳ ባለተስፋና የእግዚአብሔር ልጆች አድርጎናል፡፡
በየዕለቱ ኑሮአችን ደግም በመንፈስ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነትከኛ ጋር በመኖር ለእኛ በሚከብደን ነገር ሁሉ
ላይ አምላክነቱንና አብሮነቱን እንድናስተውል ይጠራናል፡፡

በቃል የሚጠና

“እኔ መንገድና እውነት ህይወትም ነኝ፡፡” ዮሐ14፡6

10
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 1.7:” እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ››

የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ 15፡1 – 8

መግቢያ፡- ባለፈው ኢየሱስ በምድራዊ ህይወቱ መጨረሻ ሊደርስበት ያለውን ለሐዋሪያቶቹ ከተናገረና አብሮአቸው
ከበላ በኋላ ሊመጣ ያለው ነገር እንዳያውካቸውና ማንነቱንና አብሮነቱን “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ”
ብሎ ሲያስረዳቸው ተመልክተን ነበር። በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ኢየሱስ “እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ “ሲል ምን
ማለቱ እንደሆነ በዝርዝር እናያለን ፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በዚህ ክፍል ውስጥ በቁ 1 ና 2 ላይ የምንመለከታቸው የተዘረዘሩ ነገሮች ምን እና ምን ናቸው? ምን ዓይነት


ተግባራትስ ተጠቅሰዋል?
2. ከቁ 1 – 3 ባለው ክፍል ውስጥ ስለ ተዘረዘረው ሃሳብ ምንን እንረዳለን?
3. በቁ 4 – 5 ባለው ክፍል ግንኙነትን እና ውጤትን በተመለከተ ያለእኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም ተብሎ
የተገለፀውን ሃሳብ ተወያዩበት ፡፡
4. በቁ.6 ላይ በእኔ የማይኖር ቢሆን የሚለውን ቃል እንዴት ትመለከተዋለህ/ለሽ? የሚናገረውስ ስለማን
ይመስልሃል/ሻል ውጤቱስ ምንድን ነው?
5. ቁ 7ትን እና 8ትን በማንበብ ተወያዩበት እንምንረዳው የመጨረሻው ግቡ (ውጤቱ) ጌታ ሲናገር በቁ. 8 ላይ
ምን ይላል?

ከሕይወት ጋር ማዛመድ

6. የሕይወትን ወይንም የህያውነትን ምስጢር ጌታ ሲናገር ከራሱ ጋር አያይዞ ነው የገለፀው: በዚህ ክፍል
የቅርጫፎች እና የግንዱ በአንድ መኖር (መሆን) እኔ በእናንተ እናንተም በኔ ብሎ ሲገልጽ ከዚያ ውጪ ግን
ሕይወት እንደሌለ አስተዋላችሁን?
7. ፍሬ ማፍራት የሚቻለው ሕይወት በግንዱ (በጌታ ላይ) በመሆን/በመደገፍ መሆኑንና ፍሬያማ ሕይወት
ሲኖረን ደግሞ ጌታ በዚህ ደስ እንደሚሰኝ እና አብዝተንም እንድናፈራ ይበልጥ እንደሚጠያራን ምን ያህል
ተረዳን?

ማጠቃለያ

በዚህ በያዝነው ምድራዊ ጉዞ ህይወት የሰጠንን ጌታ ተደግፈን በቃሎቹ ብንኖር ከራሳችን አልፈን ለብዙዎች ለበረከት
እና ለህይወት ምክንያት መሆን እንችላለን፡፡ ከእርሱ ውጪ ግን ሆነን ፍሬ ማፍራት የማይቻል ከመሆኑም በላይ
የሰው ልጅ ወደ ጥፋት ያውም ወደ ዘላለም ጥፋት ያመራል፡፡ አባቴ በዚህ ይከብራል ባለው መሰረት ጌታን ለማክበር
መኖር ትልቀ ዕድል ነው!

በቃል የሚጠና

” ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል፡፡” ፡ዮሐ15፡5

11
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ክፍል ሁለት: ከኢየሱስ ተዓምራቶች ውስጥ ሰባቱ

መግቢያ፡- ሐዋርያው ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስ ከሾማቸው ሐዋሪያት አንዱና ይልቁንም ጌታም ለየት ባለ መንገድ
ይወደው እነደነበር ራሱ ዮሐንስ በ21ኛው ምዕራፍ ላይ ቁጥር 20 ገልጾልናል፡፡ ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር
ላይ ሳለ ያደረጋቸውን ተዓምራት ሁሉ ተከታትሎ ያየ ህያው ምስክርም (ቁ 24) እንደሆነ ገልጦልናል፡፡ እንዲያውም
ጌታ ከቁጥር በላይ ድንቅ ተዓምራቶችን እንዳደረገና ሁሉንም ለመጻፍ ዓለም ራሱ መጻህፍቶችን ለመያዝ
እንደማያበቃ እገምታለሁ ሲል በመጽሀፉ መጨረሻ በሆነው በም 21፡25 ላይ አስፍሮልናል፡፡ የዩሐንስ ወንጌል
ከሌሎቹ ወንጌላት (Synoptic Gospels) ለየት ባለመንገድ የጌታን አገልግሎት ይገልጽልናል፡፡ ጌታ የሚያስተምረውን
ቃል በድንቅና በተዓምራት ያጸና እንደነበር በማር 16፡20 ላይ እናያለን፡፡ ስለዚህም ዮሐንስ በጻፈው ወንጌል ላይ
በመጀመሪያዎቹ ምዕራፎች 7 ጌታ ኢየሱስ ያደረጋቸውን ተዓምራቶች እናገኛለን፡፡ እነዚህም እንደሚከተሉት ፡-

2.1. የምልክቶች መጀመሪያ /የኢየሱስ ስልጣን በዓይነት ላይ/Miracle of Quality/


2.2. የሹሙ ልጅ ፈውስ /የኢየሱስ ስልጣን በርቀት ላይ /Authority of Jesus over Distance/
2.3. የቤተ ሳይዳው ፈውስ/የኢየሱስ ስልጣን በጊዜ ላይ/Authority of Jesus over Time/
2.4. አምስት ሺ ህዝብ መመገቡ/የኢየሱስ ስልጣን በመጠን ላይ/ Miracle of Quantity/
2.5. በውኃ ላይ መራመዱ/የኢየሱስ ስልጣን በተፈጥሮ ላይ/Authority of Jesus over Nature/
2.6. ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደው ሰው ፈውስ/ የኢየሱስ ስልጣን በማንኛውም ድውይ ላይ
/Authority of Jesus over any Illness/
2.7. የአልዓዛር ከሞት መነሳት /የኢየሱስ ስልጣን በሞት ላይ/Authority of Jesus over Death/
የሚሉት ናቸው ፡፡

ዮሐንስ እነዚህን ተዓምራቶች በማስፈር ኢየሱስ እርሱ መሲህ (ክርስቶስ) እና የህያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ
ሰው ሁሉ ያምን ዘንድ (20፡30) ያደፋፍረናል፡፡ እንግዲህ በእነዚህ ተከታታይ 7 ጥናቶች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ
በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች በመዘዋወር ያደረጋቸውን የተለያዩ ተዓምራቶች (ምልክቶች) ደቀመዛሙርትና ሰዎች ሁሉ
በእርሱ እንዲያምኑ ሲያደርጋቸው እናያለን፡፡ እኛም እነዚህን ጥናቶች በጋራ ስንመለከት ዛሬም ይህ ጌታ ህያው
እንደሆነና በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታዎች ላይ ስሙ ታላቅና ድንቅ ተዓምራት ሊያደርግ አቅም እንዳለው (ረዕይ
21፡5) እንድናምንና ለሌሎች ምስክር እንድነሆን (ወደ መንግስቱ እንድናፈልስ) እግዚአብሔር እንደረዳን ጸሎታችንና
ምኞታችን ነው፡፡ እግዚአብሔር ቃሉን ይባርክልን!

12
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 2.1: የምልክቶች መጀመሪያ /የኢየሱስ ስልጣን በዓይነት ላይ/Miracle of Quality/

የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ 2፡ 1 – 11

መግቢያ፡-በዛሬው የክፍል ሁለት መጀመሪያ በሆነው ጥናታችን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላው ሰርግ ላይ
በመገኘት ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ በመለወጥ ያደረገውን የታምራዊ ምልክቶች መጀመሪያ የሆነውን የሆነውን
ታምር በዝርዝር እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በዚህ ሰርግ ላይ የታደሙት እነማን ነበሩ? ሠርጉ እየተከበረ ባለበት ወቅትስ ምን ችግር ገጠማቸው?
2. የጌታ እናት ማርያም ጌታን ምን ጠየቀችው? የጌታስ ምላሽ ምን ነበር?
3. በቁ.5 ላይ ማርያም ለአገልጋዮቹ ምን አለቻቸው? አገልጋዮቹስ ምን አደረጉ? በቁ.7 ላይ ኢየሱስስ
አገልጋዮችን ምን አዘዘ?
4. አሳዳሪው የወይን ጠጁን በቀመሰ ጊዜ ሙሽራው ጠርቶ ምን አለው?
5. ጌታ የተዓምራት ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን በቃና ዘገሊላ ማድረጉ በደቀ መዛሙርቱ ላይ ያመጣውን
ለውጥ አብራራ፡፡

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. በወንጌል ስርጭት አገልግሎት ላይ የተዓምራት አስፈላጊነት ምን ያህል ተረዳህ?


7. ማርያም “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" ባለችው መሰረት አገልጋዮቹ ጌታን ታዘው ካላቸው አንዳች ሳያጎድሉ
ወይንም ሳይጨምሩ ማድረጋቸው የጌታን ክብር እንደገለጠ ዛሬም አንተ/ቺ የጌታን ቃል እንዴት ባለው
መንገድ እየተዛዝክ ነው? ለቡድኑ አካፍል፡፡

ማጠቃለያ

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የድንቅና የታዓምራት አምላክ ነው፡፡ ህይወታችን በእርሱ ባለው እምነት የተሞላ ሲሆንና ለቃሉ
የተገዛ ህይወት ስንመራ በህይወታችን የእርሱ ድንቅና ተዓምር መገለጥ ይጀምራል፡፡ ባለቀለትና በሚስያሰደነግጥ
ነገር ላይ ተገልጦ የማዳኑን ሀይል በህይወታችን ሊገልጥ ዛሬም በስራ ላይ ነው ፡፡

በቃል የሚጠና

“የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” ዮሐ 2፡5

13
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 2.2: የሹሙ ልጅ ፈውስ /የኢየሱስ ስልጣን በርቀት ላይ /Authority of Jesus over Distance/

የጥናት ከፍል፡ ዮሐ 4፡ 46 –54

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተዓምራት ሁሉ መጀመሪያ የሆነው ተዓምር በቃና ዘገሊላው ሰርግ
ላይ በመገኘት ውኃውን ምርጥ ወደሆነ የወይን ጠጅ ሲለውጥ ተመልክተን ነበር ፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ
ኢየሱስ የመጀመሪያ ምልክት ወዳረገበት ወደዚሁ ቃና ገሊላ በመመለስ ለሞት በሚያደርስ ደዌ በቅፍርናሆም ታሞ
የነበረውን የሹም ልጅ ቃል ብቻ በመናገር ሲፈውሰው እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በክፍሉ መሠረት ጌታ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ለስንተኛ ጊዜ መምጣቱ ነበር? ከዚህስ ጉዞው በፊት የት ነበር?
2. ይህ ሹም የነበረበት ችግር ምን ነበር? ኢየሱስንስ ምን ለመነው? የኢየሱስ የመጀመሪያ ምላሽ ምን ነበር?
3. ሹሙ በድጋሚ ምን ለመነው? ጌታስ እንዴት መለሰለት? የጌታን ቃል ከሰማ በኋላስ ምን አደረገ? ከዚያስ
ምን ሆነ?
4. የልጁን መፈወስ ሊያበስሩት በመንገድ ላይ የተገናኙት ሰዎች ምን አሉት? እርሱስ? በዚህ ስለዚህ ሰው
እምነት ምን ትረዳለህ?
5. ይህ ተዓምር በዚህ ሰው ቤት ውስጥ ምን ለውጥ አመጣ?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. ይህ ሹም ጌታ ወደ ቤቱ መጥቶ እጅ በመጫን ልጁን እንዲፈውስለት ጌታን ሲማፀን ጌታ ግን ብላቴናው


በህይወት አለ ሂድ ሲለው ሹሙ የጌታን ቃል በእውነት አምኖ መሄዱ ያመጣውን ለውጥ ስትመለከት
አንተስ ጌታን ታዘህ በመውጣት በህይወትህ (በቤትህ) የሆነ ተዓምራት ካለ አካፍል፡፡
7. ጌታ ኢየሱስ “ምልክትና ድንቅን ነገርን ካላያችሁ ከቶ አታምኑም” እንዳለው ዛሬ በጌታ ቤት ውስጥ
ስትመላለስ “ምልክትና ድንቅ” በአንተና በሌሎች እምነት ላይ ምን አይነት ተጽእኖ አለው ትላላህ?

ማጠቃለያ

በዘመናት ሁሉ መካካል ድንቅን እየሰራ እስከዛሬ ራሱን ያለ ምስክር ያልተወ አምላክ ዛሬም በህይወታችን በራሱ
ጊዜና መንገድ ክብሩን ሊገልጥ ይወዳል፡፡ ሆኖም እኛ ካልፈቀድንለትና ለቃሉ ካልታዘዝን የእርሱን ድንቅ ስራ ማየት
አንችልም፡፡ ዛሬም በተጨነቅንበትና በፈራንበት ነገር ሁሉ ላይ ስሙን ብንጠራ ጆሮው ከመስማት እጁም ከማዳን
እንዳለጠረች እናውቃለን፡፡ ክብር ከዘላለም እስከ ዘላላም ለእርሱ ይሁን፡፡

በቃል የሚጠና

“ኢየሱስ የነገረውን ሁሉ አምኖ ሄደ” ዮሐ 4፡51

14
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 2.3: የቤተ ሳይዳው ፈውስ/የኢየሱስ ስልጣን በጊዜ ላይ/Authority of Jesus over Time/

የምንባብ ክፍል ዮሐ 5፡ 1 – 15

መግቢያ፡-ባለፈው ጥናት በቅፍርናሆም ለሞት በሚያደርስ በሽታ የነበረውን የሹም ልጅ ጌታ ኢየሱስ ቃል ብቻ


ተናገሮ “ሂድ ልጅህ በህይወት አለ” በማለት ሲፈውሰውና ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ኢየሱስ ወደ
ኢየሩሳሌም ተመልሶ ቤተሳይዳ በምትባል መጠመቂያ ቦታ “ሰው የለኝም ብሎ” ለ38 ዓመት የአልጋ ቁራኛ የነበረውን
ሰው “ተነሳና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” ብሎ ሲፈውሰውና በሽተኛው ተነስቶ አልጋውን ተሸክሞ ሲሄድ እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ስለ ቤተሳይዳ መጠመቂያ የተከማቹት ህዝቦች ምን ዓይነት ነበሩ? ምንን ፍለጋ ነበር የተከማቹት? ፈውስን
የሚያገኙትስ እንዴት ባለው መንገድ ነበር?
2. በመጠመቂያው ሊፈወስ የሚችል ሰው ምን ዓይነት ነበር? ሁሉንስ ዓይነት በሽታ ይፈውስ ነበርን?
3. በቁ. 5 ና 6 ላይ ኢየሱስ ማንን በመገናኘት ነበር ወደዚህ የመጣው? የነበረበት ችግርስ ምን ነበር? ለምን
ያህል ጊዜ? ለብዙ ዘመን በዚህ ቦታ ተቀምጦ ያልተፈወሰበት ምክንያት ምን ነበር?
4. ጌታ ኢየሱስ ይህ ሰው ምንን ፈልጎ ወደዚህ መጠመቂያ እንደመጣ እያወቀ “ልትድን ትወዳለህን?” ብሎ
መጠየቅ ለምን አስፈለገው? ብዙ ፈውስን ሚፈልጉ ሰዎች በዙርያው አያሉ ለምን ይህንን ብቻ?
5. በቁ.8 ላይ ኢየሱስ በሥልጣን ቃል “አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” ካለው በኋላ ምን ሆነ? በተፈወሰው ሰው ላይ
ከአይሁድ የደረሰበት ተቃውሞ ምን ነበር? ዳግመኛ ኢየሱስን በቤተ መቅደስ በተገናኘው ጊዜ ጌታ ምን
አለው?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. የተፈወሰው ይህን ሰው ያዩት ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ሊላቸው ሲገባ ተቃውሞ ማድረጋቸው ለምን


ይመስልሃል/ሻል? ለሕወታችንስ ምን ያስተምረናል
7. ኢየሱስ ተስፋ ለቆረጡና የሚረዳቸው ለሌላቸው ፈጥኖ ደራሽና ከችግር ነፃ የሚያወጣ ጌታ መሆኑን ምን
ያህል ተረዳህ(ሽ)? አንተስ እንደዚህ አይነት ሰዎች ቢያጋጥሙህ በምን ዓይነት መንገድ ልትረዳ ትችላለህ?

ማጠቃለያ

አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ ከጎናችን ሆኖ የሚያፅናናን ሠው፤ በችግራችን አይዞህ ባይ
እንፈልጋለን፡፡ይሁን እንጂ ስጋ ለባሽ በራሱ ሁኔታ ስለተጠመደ የራስ የሚሆን ችግርን ተረድቶ ከጎን የሚቆም
በሚታጣበት ጊዜና ፍፁም ብቸኝነት በተሰማን ወቅት ጌታ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንዳለና ካለንበት ችግርና የኑሮ
እንቆቅልሽ ነፃ ሊያወጣን የሚችል ፈፁሞ ፍቅርን የተሞላና ሩህሩህ አዛኝ ወዳጅ እንዳለን ፈፅሞ መዘንጋት የለብንም፡
እርሱ ራሱ “እናት የወለደችውን ትረሳ ይሆናል፤ እኔ ግን ፈጽሞ አልረሳሽም” ብሎ ቃል ገብቷልና፡፡

በቃል የሚጠና

“ተነሳና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡፡” ዮሐ5፡9

15
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 2.4: አምስት ሺ ህዝብ መመገቡ/የኢየሱስ ስልጣን በመጠን ላይ/ Miracle of Quantity/

የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ 6፡5 – 14

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ለ38 ዓመት ሙሉ በደዌ የተመታውን የአልጋ ቁረኛና ሰው የለኝም ብሎ ተስፋ
የቆረጠውን ሽባ ሰው በኢየሩሳሌም ቤተሳይዳ መጠመቂያ ጌታ እንደፈወሰውና አልጋውን ተሸክሞ በደስታ እንደሄደ
ተመልክተን ነበር ፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ኢየሱስ በምድረበዳ የተራበውን አምስት ሺህ ሕዝብ ሁለት ዓሳና
አምስት እንጀራ ብቻ በማብዛት በተዓምር ሲመግብ በዝርዝር እናያለን።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በቁ 5 ላይ ኢየሱስ አይኖቹን አንስቶ ምን አየ? ከዚያስ ፊሊጶስን ምን ጠየቀው? ለምን? የፊሊጶስስ ምላሽስ
ምን ነበር?
2. የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ምን መፍትሄ አመለከተ? መፍትሄው ከእርሱ አንጻር በቂ ነበርን?
3. ጌታ ኢየሱስ ህዝቡ እንዲቀመጡ ደቀ መዛሙርቱን ካዘዘ በኋላ ምን አደረገ?
4. አመስግኖ ለደቀ መዛሙርቱ መስጠቱ ምንን ያመለክተናል? ተዓምራቱ በኃዋሪያት እጅ በምን ዓይነት
መንገድ ተገለጠ?
5. ህዝቡ ሁሉ በሚፈልጉት መጠን (ቁ 11) ከተመገቡና ከጠገቡ በኋላ ምን ሆነ?
6. ጌታ ኢየሱስ ግን ይህ ህዝብ የበሽተኞችን ስለፈውስና ተዓምራቶችን ስላየ ብቻ (ቁ 2 - 3) እንደተከተለው
እያወቀ ሌላ ተዓምራት በማድረግ መመገቡ ስለጌታ ፍቅር ምን ያስተምርሃል? ህዝቡስ ይህንን ተዓምር ባዩ
ጊዜ ምን አሉ?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

7. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህ ህዝብ ተዓምራትን ስላየ ብቻ እንደተከተለው እናያለን፡፡ አንተስ / አንቺስ ምን


ዓይተህ ነው ጌታን የምትከተለው?
8. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ባዶውን ነገር ሊምላ ጥቂቱን ነገር ለክብሩ በህይወትህ ሊያበዛ እንደሚችልና
በሚያስፈልገንም ነገር ሊረዳን ከእኛ ጋር እንዳለ አስተዋልክን? ባለፈውስ ዘመን በእንዲህ ሁኔታ በህይወትህ
የተገለጠበት ጊዜ ካለ ለቡድኑ አካፍል፡፡

ማጠቃለያ

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተዓምራት አምላክና ጌታ ነው፡፡ የህዝቡን መንፈሳዊ ፍላጎት ወይም ጉድለት ብቻ ሳይሆን
ስጋዊም ፍላጎቶች የሚያይና የሚሞላ በህዝቡ ደስታ ደግም ደስ የሚለው ጌታ ነው፡፡ ሐዋርያቱን “እስካሁን እኔን
ስትከተሉ አንዳች የጎደለባችሁ ነገር አለን?” ብሎ ሲጠያቃቸው “ጌታ ሆይ አንድ ስንኳ” ብለው ነው የመለሱለት፡፡
ዛሬም በጉድለታችን ሁሉ ውስጥ ተዓምራታዊ ሙላቶች ለማድረግ የሚችል ታላቅ አምላክ ነው ያለን፡፡ ክብር
ለገናናው ስሙ ዛሬም ለዘለዓለምም ለእርሱ ይሁን፡፡

በቃል የሚጠና

“ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣ ነብይ ነው፡፡” ዮሐ 6፡14

16
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 2.5: በውኃ ላይ መራመዱ/የኢየሱስ ስልጣን በተፈጥሮ ላይ/Authority of Jesus over Nature/

የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ 6፡16 – 24

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ጌታችን ኢየሱስ ይከተሉት የነበረውን አምስት ሺህ ሕዝብ ሁለት ዓሳና አምስት እንጀራ
ብቻ በድንቅ ተዓምራት ሲመገብና ህዝቡም ጠግበው ከበሉ በኋላ ደቀመዛሙርቱ 12 መሶብ እንደሰበሰቡ
ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ባስጨነቀውና ባስፈራራው
ማዕበል ላይ እየተራመደ ሲመጣና “አትፍሩ እኔ ነኝ” ሲላቸው እንመለከታን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በቁ 16 ና 17 ላይ እንደተገለጸው ደቀ መዛሙርቱ በታንኳ ገብተው ወዴት እየሄዱ ነበር? ሰዓቱስ ስንት


ነበር?
2. በጉዞ ላይ ሳሉ ምን ገጠማቸው? በዚህ ጊዜ ኢየሱስ የት ነበር?
3. በቁ 19 ላይ በጨለማ በባህር ላይ ከተገለጠው ማዕበልና ብርቱ ነፋስ በተጨማሪ የሚያስፈራ ነገር ምን
አጋጠማቸው?
4. ጌታ ኢየሱስ ባስጨነቃቸው ማዕበልና ወጀብ ላይ በስልጣን እየተራመደ ሲመጣ አይተው በፈሩ ጊዜ ምን
አላቸው?
5. ደቀ መዛሙርቱ ጌታ “አትፍሩ እኔ ነኝ” ሲላቸው ምን ሊያደርጉ ወደዱ? ጌታ ወደ ታንኳይቱ ገባን?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. ደቀ መዛሙርቱ ጌታን በዚያ በጨለማው ባህር ላይ በማዕበሉና በብርቱ ነፋስ ውስጥ እየተራመደ እንደመጣ
“እሰከ ዓለም ፍጻሜ ከእናንተ ጋር እሆናለው” ብሎ ቃል የገባው ጌታ ዛሬም በምታልፍበት ሁኔታ ሁሉ
ውስጥ ጌታ ከአንተ ጋር እንደለና ምን ያህል አስተዋልክ?
7. በማዕበሉና በወጀቡ መካክል መንገድ ያለውና እርሱ እራሱ መንገድ የሆነው ጌታ “እኔ ነኝና አትፍሩ”
የሚለው የኃይልና የእምነት ቃል ምን ያህል በህይወትህ ውስጥ እየሰራ ነው?

ማጠቃለያ

ጌታ ኢየሱስ በብዙ ማረጋገጫ ከሚያምኑት ጋር እስከዓለም ፍጸሜ ድረስ እንዳለ ተናግሯል፡፡ ይሄንንም ቃሉን
በወጀቡና በአስፈሪው አውሎ ነፋስ መካከል በመገለጥ “እኔ ነኝና አትፍሩ” እያለ ማዕበሉን ጸጥ ያደርጋል፡፡
የህይወታችንንና የመንግስቱ ስራ ባለቤት ጌታ ስለሆነ በእርሱ ታምነን ልንመላለስ ይገባናል፡፡

በቃል የሚጠና

“እኔ ነኝ አትፍሩ” ዮሐ6፡ 21

17
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 2.6: ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደው ሰው ፈውስ/ የኢየሱስ ስልጣን በማንኛውም ድውይ ላይ

/ Authority of Jesus over any Illness/

የምንባብ ክፍል፡-ዮሐ 9፡1–12

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት የጌቶች ጌታ የነገስታት ንጉስ የኃያላንም ኃያል የሆነውና በፍጥረት ሁሉ ላይ ሙሉ
ስልጣንና ኃያል ያለው ጌታ በውሀ ላይ እየተራመደ ደቀ መዛሙርቱን “አይዟችሁ እኔ ነኝ” ሊላቸው እነርሱም
በመገረምና በመደነቅ በፍርሃትም ተሞልተው እንደነበር ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ከመወለዱ
ጀምሮ ለብዙ ዘመን ማየት የተሳነውን ሰው ሲፈውስ እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ጌታ ሲያልፍ ያየውን ስለዚህ ሰው ደቀ መዛሙርቱ ጌታን ምን ብለው ጠየቁት? የጌታስ ምላሽ ምን ነበር?
2. “የእግዚአብሔር ስራ በእርሱ እንዲገለጥ እንጂ” ሲል ጌታ ምን ማለቱ ነው? (ተወያዩበት)
3. “ቀን ሳለ የላከኝን ስራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች፡፡” ሲል ምን ማለቱ
ነው?
4. ኢየሱስ እንዴት ባለው መንገድ ይህን ሰው ፈወሰው? ከሌሎቹ የፈውስ መንገዶች የሚለየው እንዴት ነው?
“በዓለም ሳለው የዓለም ብርሃን ነኝ” ብሎ ይህን ሰው መፈወሱ ምን ያሳይሃል፡፡
5. ይህ ሰው ከተፈወሰ በኋላ እርሱን የሚያውቁት ሰዎች (ጎረቤቶቹ) ምን አሉ?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. በምንም መንገድ ያልተፈወሰ ችግር ወይም በሽታ የጌታን ክብር እንዴት ሊገልጽ እንደሚችል አስረዳ፡፡
7. የዓለም ብርሃን የሆነው ኢየሱስ ለመንፈሳዊ ዓይነ ስውርነት ብቻ ሳይሆን በስጋም ማየት ለተሳነው
ብርሃንን ሊሰጥ እንደሚችል ተረዳህን?
8. ጌታ ራሱ ቀን ሳለ (ጊዜዬ ሳይደርስ) ቶሎ ብዬ የላከኝን ስራ ማድረግ ይገባኛል ካለ አንተስ የጌታ ዳግም ምጻቱ
በጣም በተቃረበበት የመጨረሻው ጊዜ ላይ የእርሱን ስራ ለማድረግ ምን ያህል እየተጋህ ነው?

ማጠቃለያ

የዓለም ብርሃን ኢየሱስ በምድር በስጋ በነበረበት ጊዜያት ሁሉ የሰው ልጆችን ስጋዊና መንፈሳዊ እንቆቅልሾችን
እየፈታ ነጻነትን እያወጀ የእግዚአብሔርን መንግስት ለሰው ልጆች አሳይቷል፡፡ ዛሬም በስጋም በመንፈስም ለታወሩ
(ማየት ለተሳናቸው) እውነተኛው ብርሃን እርሱ ጌታ ኢየሱስ ነው፡፡ እኛም የእርሱ አምባሰደሮች እንደሆንን የእርሱን
አዳኝነትና ብርሃንነት (ለስጋ፣ ለነፍስና ለመንፈስ) በዚህ ጨለማ አለም ለሚኖሩ ሁሉ በየዕለቱ መናገር እንዳለብንና
ወደ መንግስቱም እንዲፈልሱ በጸሎት እየተጋን መርዳት እንዳለብን ቃሉ ያስተምረናል፡፡

በቃል የሚጠና

“ቀን ሳለ የላከኝን ስራ ላደርግ ይገባኛል፡፡ ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች፡፡” ዮሐ 9፡4

18
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 2.7: የአልዓዛር ከሞት መነሳት /የኢየሱስ ስልጣን በሞት ላይ/Authority of Jesus over Death/

የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ 11፡ 1 – 45

መግቢያ፡- ባለፈው ባለፈው ጥናት ከመወለዱ ጀምሮ ማየት የተሳነውን ሰው በሚያስገርምና ለየት ባለመንገድ ጌታ
ሲፈወስ ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ የማርታና የማርያም ወንድም የሆነውና ጌታም ይወደው
የነበረው ዓልዓዛር ከሞተና ከተቀበረ ከ4 ቀናት በኃላ ጌታ በመለኮታው ኃይሉ ከሞት ሲያስነሳውና ከመቃብር
በሕይወት ሲወጣ እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ማርታና ማርያም ወንድማቸው ዓልዓዛር በታመመ ጊዜ ምን አደረጉ? ኢየሱስ መልዕክቱ በደረሰው ጊዜ


ምን አለ? ከዘያስ ምን አደረገ?
2. በቁ 7 ላይ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ይሁዳ እንሄዳለን ባላቸው ጊዜ ምን መለሱለት? ጌታስ ምን
አላቸው?
3. ጌታ ኢየሱስ ዓልዓዛር ሳይሞት ሊመጣ ያልወደደበት (እስኪሞት) የዘገየበት ምክንያት ምን ነበር?
4. ማርታ ጌታ ወደ መንደራቸው እንደመጣ በሰማች ጊዜ ምን አደረገች? የጌታስ ምላሽ ምን ነበር? ጌታ ኢየሱስ
ዓልዓዛርን ከሞት እንደሚያስነሳው እያወቀ ስለምን አለቀሰ? መንፈሱስ ስለምን ታወከ?
5. ወደ መቃብሩ በደረሱ ጊዜ ጌታ ምን አዘዛቸው? ማርታስ ምን አለችው? ጌታስ ምን መለሰላት?
6. ጌታ ኢየሱስ ምን ብሎ ጸለየ? የጸሎቱ ዓላማ ምን ይመስልሃል? ከዚያስ ምን ሆነ?
7. የዓላዓዛር ከሞት መነሳት ከነ ማርያም ጋር በነበሩት አይሁድ ላይ ምን ለውጥ አመጣ? (ቁ 45)

ከህይወት ጋር ማዛመድ

8. ባጠናነው ክፍል መሰረት ጌታ በጠበቅከው ሳይሆን በራሱ ጊዜ ተገልጦ ያደረገልህ ተዓምር ካለ ለቡድኑ
አካፍል፡፡
9. ከእግሩ ስር ሁሌም በመገኘት ከአፉ ቃል ትማር የነበረችው ማርያም ለቅሶዋ የጌታን ልብ እንደነካና
እንባውን እንደፈሰሰ ዛሬ ከጌታ ጋር ያለህ የቃል ህይወት ምን ይመስላል?

ማጠቃለያ

ጌታ ኢየሱስ እውነተኛ ወዳጅና የልጆቹን ህመም፣ ችግርና መከራ የሚያይና የሚረዳ ለሞተ ነገራችን ህይወት
የሚሰጥ የትንሳኤ ጌታና ንጉስ ነው፡፡ ሰው የሰራውን ሰው ሊፈታ ይችላል ህይወትን ሊሰጥ የሚችል ግን እርሱ ጌታ
ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ እኛም ሁልጊዜ በእምት እንደፈቃዱ የማዳኑን ኃይል በህይወታችን ሊገለጥ የታመነና ጻድቅ
አምላክ ነው፡፡

በቃል የሚጠና

“ትንሳኤና ህይወት እኔ ነኝ፡፡ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፡፡” ዮሐ 11፡ 25

19
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ክፍል ሦስት: ወደ ኢየሱስ ከቀረቡ ሰዎች መካከል ሰባቱ

መግቢያ፡-ሐዋርያው ዮሐንስ የዘገባቸውን ሰባቱን የጌታ ኢየሱስ ተዓምራቶች በክፍል ሁለት ላለፉት ሰባት ተከታታይ
ጥናቶች ተመክለን ነበር። በዚህ ክፍል ሶስት ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሦስት ዓመት ተኩል የምድር
አገልግሎቱ ወቅት በተለያየ ጊዜና ምንክያት ወደ እርሱ ቀርበው በአስደናቂ ሁኔታ ሕይወታቸውን የለወጠላቸው
በርካታ ሰዎች በወንጌላት ውጥስ ተዘግበው የሚገኙ ቢሆንም በጥናቱ መግቢያ ላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ካለን
የጊዜ ውስንነት የተነሳ ለዚህ አጭር ጥናት ዓላማ አንጻር ለትምህርታችን ይጠቅም ዘንድ ለመነሻ ያህል ከወንጌላት
ውስጥ ሰባቱን ሰዎች ብቻ እንመልከታለን።

እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡-

ጥናት 3.1 በአጋንንት የተያዘው ሰው


ጥናት 3.2 ለአስራ ሁለት ዓመታት ደም ይፈሳት የነበረች ሴት

ጥናት 3.3 ኢየሱስን ሽቱ የቀባች ኃጢአተኛ ሴት


ጥናት 3.4 ቀረጥ ሰብሳቢው ዘኬዎስ

ጥናት 3.5 የሕግ መምህሩ ኒቆዲሞስ


ጥናት 3.6 ሳምራዊቷ ሴት
ጥናት 3.7 በምንዝር የተያዘች ሴት

20
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 3.1: በአጋንንት የተያዘው ሰው

የምንባብ ክፍል፡-ማር 5፡1–20

መግቢያ፡-ባለፈው ጥናታችን የክፍል ሁለት ማጠናቀቂያ የነበርውን ሰባተኛ ጥናት ስለ ዓልዓዛር ከሞት መነሳት
ተመልክተን ነበር። በዛሬው የክፍል ሦስት መጀመሪያ በሆነው ጥናታችን ደግሞ ለብዙ ዘመን በአጋንንት ተይዞ
የነበረውን ሰው ጌታ እንዴት ነፃ እንዳወጣውና ህይወቱን እንደቀየረው እናያለንን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ጌታ ይህንን ሰው ሲያገኘው ሰው የውየነበረበት የህይወት ሁኔታ ምን ይመስል ነበር? ማር5፡ 1 – 5 ከሉቃ 8፡


27 ጋር በማዛመድ ተወያዩበት፡፡
2. ለአካባቢው ነዋሪዎች እጅግ አስቸጋሪና አስፈሪ የነበረው ይህ ሰው ጌታን ሲያይ ምን አደረገ? ቁ.6
ይህ ድርጊቱ የኢየሱስን የበላይነት እንዴት ያሳያል?
3. በዚህ ሰው ውስጥ የነበሩት ብዙ ሺህ አጋንንት/ሌጊዮን ከከተማው ጌታ እንዳያወጣቸው መለመናቸው
ለምን ይመስልሀል? ቁ10 የእሪያ መንጋንስ ለምን መረጡ? ቁ. 11 ከዘሌዋውያን 11፡7 ጋር አዛምድ፡፡
4. ጌታ እርኩሳን መናፍስቶችን ከሰውየው ካስወጣቸው በኋላ በሰውዬው ህይወት ውስጥ ምን ለውጥ ታየ?
ከቁ. 15 – 20

ከህይወት ጋር ማዛመድ

5. ጌታ ወደ ጌርጌሴኖን ሄዶ ያደረገው ነገር ይህንን ሰው ነፃ ማውጣት ብቻ ነበር፡፡ ይህንን ስታይ ዛሬም ጌታ


ለታሰሩት ግድ እንደሚለው አወቅህ/ሽ አንተ/ቺ ምን ያህል ላልዳኑት ትፀልያለሽ/ህ?
6. ዲያቢሎስ ክፉና ጨካኝ መሆኑን አወቅህ ምን ያህል ትቃወመዋለህ? እንዴትስ ነው የምትቃወመው?
ያዕቆብ 4፡ 7–8

ማጠቃለያ

እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ለማዳን የሄደበት መንገድ አንድያ ልጁን እስከመስጠት የደረሰ ነው፡፡ በልጁ ያመነ ሁሉ
የዘላለም ህይወት ያገኝ ዘንድ ጌታ የመዳን በሩን ክፍት አድርጎት እያለ ዛሬም ግን ብዙዎች በአጋንንት እስራት ውስጥ
ተይዘው ይገኛሉ፡፡ ስለ እነዚህ ሰዎች ግድ ብሎን ልንፀልይና ወንጌልን ልንመሰክር ይገባል፡፡

በቃል የሚጠና

“ወደ ቤትህ በቤተ ሰዎችህ ዘንድ ሄደህ ጌታ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገልህ እንዴትስ እንደማረህ አውራላቸው
አለው።” ማር 5፡19

21
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 3.2: ለአስራ ሁለት ዓመታት ደም ይፈሳት የነበረች ሴት

የምንባብ ክፍል፡-ማር 5፡25 – 34

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ለብዙ ዘመን በአጋንንት ተይዞ የነበረውን ሰው ጌታ እንዴት ነፃ እንዳወጣውና ህይወቱን
እንደቀየረው ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ለአስራ ሁለት ዓመታት ደም ሲፈሳት የኖረችውንና ለባለ
መድኃኒቶች ያላትን ሃብትና ንብረት ሁሉ ብትጨርስም ለችግርዋ ምንም ዓይነት መፍትሄ ሳታገኝ የነበርችን ሴት
ከጌታ አስደናቂ የእምነት ፈውስ ሲሆንላት እናያለን፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ኢየሱስን እያጨናነቀ ከነበረው ብዙ ህዝብ መሃል የተጠቀስችዋ ሴት የ12 ዓመታቱን ደም መፍሰስ


ለማስቆም ያደረገቻቸው ጥረቶች ምን ነበሩ? ምንስ መፍትሄ አስገኙላት?
2. ስለ ኢየሱስ ሰምታ በሰዎች መሃል ከበስተ ኋላው መጥታ ልብሱን የዳሰሰችው ምን ስላመነች ነበር? ይህስ
እርምጃዋ ምን አስገኘላት?
3. ለዘመናት ሲያሰቃያት ከነበረው መከረዋ በዛው ቅጽበት መዳንዋን ለዚች ሴት መጀመሪያ ማን ነገራት?
4. ኢየሱስ ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው ብሎ ለጠየቀው ጥያቄ የደ ማዛሙሩ ምላሽ ምን የሚል ነበር?
5. ኢየሱስ ያደረገችውን ዘውር ብሎ ይመለከት በነበረት ሁኔታ” የተደረግላትን በሰውንቱዋ ያወቀችዋ “ይህች
ሴት ወደ ኢየሱስ የቀረበችው በእንዴት ዓይነት አኳሃን ነበር? ኢየሱስስ ምን ኣላት?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. የዚህች ሴት ፈውስ ስለ ኢየሱስ የጸጋና የሕይወት ምንጭነት ምን ያስረዳናል?


7. ምንም እንኳ ብዙ ሰዎች በኢየሱስ አጠገብ ወይም ዙሪያ ሆነው ስፍራውን ቢያጨናንቁትም ይህች ሴት
ብቻ በእምነት ኢየሱስን መዳሰስዋና ፈውስን መቀበልዋ ምን ያስተምረናል?

ማጠቃለያ

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም እንደ ጥንቱ ክንዶቹ የሚሰሩ፣ አይኖቹ የሚያዩ፣ ልቡ የሚራራና
በጠራነውም ጊዜ የሚሰማን አምላክ እነደሆነ በመረዳት እነደዚህች ሴት ብዙ መሰናክሎችን አልፈን ወደ እርሱ
በእምነት ሁል ጊዜ ብንቀርብ በሕይወታችን ብዙ ድንቆችን ያደርግልናል።

በቃል የሚጠና

“እርሱም ልጄ ሆይ እምነት ሽ አድኖሻል በሰላም ሂጂ ከሥቃይሽም ተፈወስ ሽ አላት። ማር 5፡34

22
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 3.3 ኢየሱስን ሽቱ የቀባች ኃጢአተኛ ሴት

የምንባብ ክፍል፡- ሉቃ7፡36 – 50

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ለአስራ ሁለት ዓመታት ያህል ደም ሲፈሳት የኖረችውንና ለባለ መድኃኒቶች ያላትን
ሃብትና ንብረት ሁሉ ብትጨርስም ለችግርዋ ምንም ዓይነት መፍትሄ ሳታገኝ የነበርችን ሴት ከጌታ አስደናቂ የእምነት
ፈውስ ሲሆንላት ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ አንዲት በኃጢአትዋ በከተማው የምትታወቅ ሴት
ጌታ ኢየሱስ ወደ ተጋበዘበት ፈሪሳዊ ቤት በመገኘት የሽቱ ስጦታ ይዛ መቅረቡዋንና ያደረገችውን፣ በዚያም
ሕይወትዋ በጌታ እንዴት እንደዳነ እናያለን፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ኢየሱስ ፈሪሳዊው ቤት ለማዕድ መጋበዙን ሰምታ ለኢየሱስ የአልባስጥሮስ ሽቱ ያመምጣችለት የዚያ


ከተማ ሴት በክፍሉ የተገለጠችበት መለያዋ ምን የሚል ነው? ትክክለኛ መጠሪያ ስምዋ ማን የምትባል
ይመስልሃል/ሻል?
2. ያመጣችውንስ ሽቱ ለኢየሱስ በእንዴት ዓይነት ሁኔታ አበረከተችለት? የጋበዘው ፈሪሳዊ የሴቲቱን ድርጊት
ተመልክቶ ስለ ኢየሱስ በልቡ ያሰበው ምን ነበር?
3. ኢየሱስ ለጋባዡ የልብ ሃሳብ እርሱ በቤቱ ለኢየሱስ ያደረገውን ሴቲቱ ካደረገችው ጋር በማነጻጸር ከቁ 40-47
ባለው ኢየሱስ ለስምኦን የተናገራቸውን በርዝር ተወያዩበት ።
4. ኢየሱስ ለሴቲቱ መለያዋ ስለነበረው ኃጢአትዋ በቁ 48 ላይ ምን ብሎ ተናገራት? ይህንን የኢየሱስን ንግር
የሰሙት ተጋባዦች በልባቸው ያስቡት የጀመሩት ምን በማለት ነበር?
5. ኃጢአትን ማስተሰረይ ማለት ምን ማለት ነው? ይህንንስ ማደርግ የሚችለው ማን ብቻ ይመስልሃል/ ሻል?
6. ኢየሱስ ለዚያች በኃጢአትዋ ትታወቅ ለነበረች ሴት ያደረገላት የመጨረሻ የስንብት ቃል ምን የሚል ነበር?
ጋባዡ ፈሪሳዊው ስምኦን ሆኖ ሳለ የዚችን ሴት ነጻ መውጣት ስንመለከት ኃጢአታቸውን ለሚናዘዙና
ኢየሱስን በእውነት ለሚያምኑት እርሱ ምን እንደሚሆንላቸው ነው ክፍሉ የሚያስረዳን?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

7. ኢየሱስን በቤቱ የጋበዘውን ፈሪሳዊ ስምኦንን ሳይሆን የኃጢአተኛዋን ሴት ማድነቁ ስለ ኢየሱስ ምን


ያስረዳናል? ሴቲቱስ በሰው ቤት በድፍረት ለኢየሱስ ካደረገችው ድርጊትዋ ምን እንማራለን?

ማጠቃለያ

ለኢየሱስ የምንገልጸው እውነተኛ ፍቅርና መሰጠት ቀደም ሲል በኃጢአት የነበርንበትን ሁኔታ ፣ክርስቶስ ለመስቀል
ሞት ራሱን አሳልፎ በመስጠት ለእኛ የገለጸውን ፍቃር፣ አሁን የኃጢአት ይቅርታ እንዳገኘንና ወደፊትም ይህ የፍቅር
ጌታ እኛን ዘወትር እንደሚጠብቀን በመረዳት ከልብ በመነጨ ፍቅር ውድ ነው ከምንለው ብዙ መስዋዕት ጋር በፊቱ
ልንቀርብ ይገባናል።

በቃል የሚጠና

“ሴቲቱንም ።እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ አላት።” ሉቃ7:50

23
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 3.4: ቀረጥ ሰብሳቢው ዘኬዎስ

የምንባብ ክፍል፡- ሉቃ 19፡1 – 10

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት አንዲት በኃጢአትዋ በከተማው የምትታወቅ ሴት ጌታ ኢየሱስ ወደ ተጋበዘበት ፈሪሳዊ
ቤት በመገኘት የሽቱ ስጦታ ይዛ መቅረቡዋንና ያደረገችውን፣ በዚያም ሕይወትዋ በጌታ እንዴት እንደዳነ ተመልክተን
ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ሕዝቡን ከተገቢው በላይ ቀረጥ በማስከፈል ትርፉን ለራሱ በማድረግ በሕዝቡ
ዘንድ የተናቀና የተጠላ ወደነበረው ቀረጥ ሰብሳቢው ዘኬዎስ ወደ ተባለ ባለጠጋ ሰው ቤት ኢየሱስ መግባቱንና
ለዚያም ሰው ሕይወት መዳን እንደሆነለት እናያለን፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ኢየሱስ በኢያሪኮ ሲያልፍ ባለ ጠጋው ዘኬዎስ ኢየሱስን ለማየት ቢፈልግም ቁመተ አጭር ስለ ነበር ከህዝቡ
ብዛት የተነሳ ማየት ባለመቻሉ ኢየሱስን ለማየት የወሰደው እርምጃ ምን ነበር?
2. ኢየሱስ ከስፍራው በደረሰ ጊዜ አሻቅቦ ዘኬዎስን ከሾላው ዛፍ ላይ ባየው ጊዜ ምን አለው? በስፍራው የበሩት
ሁሉ የኢየሱስን ከዘኬዎስ ቤት የመግባት ውሳኔ ተመልክተው ያጉረመረሙት ስለምን ነበር? ይህ የሆነው
የዘኬዎስን የባለጠግነት ምንጭ ምን ስለ ነበር ነው?
3. ዘኬዎስ እውነተኛ የንሳሃ ውሳኔውን ያሳየበት የበደለውን በደል በምን ዓይነት መንገድ ለመካስ ቃል
በመግባት ነበር ለኢየሱስ የተናገረው/የተናዘዘው?
4. በቁ 9 ና 10 ላይ ከኢየሱስ ምላሽ እንደምንመለከተው ለዘኬዎስ ቤት ምን ሆነለት? ኢየሱስ ዘኬዎስን
የአብረሃም ልጅ ሲልስ ምን ማለቱ ይመስልሃል/ ሻል?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

5. ኢየሱስ ስለ ዘኬዎስ ግድ ብሎት ያደረገው የወንጌል የምስራች ስንመለከት ለተናቀውም ሆነ ለተጠላ


የኅብረተሰብ ክፍል ድነት የሚያስፈልግ መሆኑን ተረድተን እንዲህ ዓይነት ሰዎች ወደ ድነት ይደረሱ ዘንድ
ለመርዳት ምን ያህል እንቀርባቸዋለን?
6. ዘኬዎስካደረገው ነገር በተለም ከሰዎች አለአግባብ የሰበሰበውን ገንዘብ ከዛች ቀን በፊት የወሰደውን እንኳ
ሳይቀር በእጥፍ ለመመለስ መወሰኑ ስለእውነተኛ ንሳሃ ውስጣዊ ብቻ ሳይሆን ውጫዊ የተግባር
እርምጃንም የሚያካትት መሆኑ ምን ያስተምረናል?

ማጠቃለያ

ቀረጥ ሰብሳቢው ዘኬዎስ ያስተዳድር የነበረው ሕዝቡን ከተገቢው በላይ ቀረጥ በማስከፈል ትርፉን ለራሱ በማድረግ
ነበር።ከዚህም የተነሳ ቀረጥ ሰብሳቢዎች በሕዝቡ ዘንድ የተናቁና የተጠሉ ነበሩ። ኢየሱስ ከስቅለቱ በፊት ባሉት ጥቂት
ቀናት እንኳ ዘኬዎስን የጠፋ በመሆኑ ድነት ስለሚያስፈልገው ለዘኬዎስ ድነት የሆነለት መሆኑ ኢየሱስ ወደ ምድር
የመጣበት ዓላማ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን እንደነበር የሚያስረዳ ነው።

በቃል የሚጠና

“የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና አለው።” ሉቃ 19፡10

24
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 3.5: የአይሁድ መመህሩ ኒቆዲሞስ

የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ 3 ፡ 1 – 24

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ሕዝቡን ከተገቢው በላይ ቀረጥ በማስከፈል ትርፉን ለራሱ በማድረግ በሕዝቡ ዘንድ
የተናቀና የተጠላ ወደነበረው ቀረጥ ሰብሳቢው ዘኬዎስ ወደ ተባለ ባለጠጋ ሰው ቤት ኢየሱስ መግባቱንና ለዚያም
ሰው ሕይወት መዳን እንደሆነለት ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ አለቃ
ወደ ጌታ በሌሊት በመሔድ በግሉ ከጌታ ጋር ያሳለፈውን ጊዜና በቆይታውም ያተረፈውን ህይወት በዝርዝር እናያለን፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ኒቆዲሞስ በቀን ሳይሆን በሌሊት ወደ ጌታ የሄደው ለምን ይመስልሃል/ሻል?


2. ኒቆዲሞስ ወደ ጌታ ሲመጣ ስለ ጌታ ማንነት የነበረው ግንዛቤ ምን ዓይነት ነበር?
3. ከጌታ ለመስማትስ ምን ያህል ዝግጁ የነበረ ይመስልሀል/ሻል?
4. በቁ. 3 ላይ ጊዜ ሳያጠፋ ኒቆዲሞስ ደግም መወለድ እንደሚያስፈልገው የተናገረው ለምንድን ነው?
5. ኒቆዲሞስ ከጌታ ጋር ካሳለፈው ጊዜ የተነሳ ህይወቱ ምን ያህል የተለወጠ ይመስልሀል/ሻል? ከዮሐ7፡50 እና
ዮሐ19፡39 ጋር በማዘመድ ተወያዩበት፡፡

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. እግዚአብሔርን በህብረት ከማምለክ ባለፈ በግል ደግም በጓዳ የጌታን ፊት የመፈለጉን ጠቀሜታ ወይም
አስፈላጊነት ተወያዩበት፡፡
7. ሰዎች ጌታ በግላቸው እንዲፈልጉት የሚያደርጋቸው ምክንያት ምን ይመስልሃል/ሻል? የእናንተስ?
ተወያዩበት፡፡

ማጠቃለያ

ኒቆዲምስ የአይሁድ አለቃ ባለስልጣንና በዘመኑም አዋቂ ሰዎች ነን ብለው ከሚሉት ከፈሪሳዉያን ወገን የነበረ
ቢሆንም ስልጣኑና ማንነቱ አካባቢውም ሳያግደው ትሁት በሆነ ማንነት ወደጌታ እንደመጣ ሁሉ እኛም ጌታን ማየት
ያለው በትህትና እና እርሱን በመፈለግ ውስጥ ብቻ እንደሆነ ሊገባን ያስፈልጋል፡፡

በቃል የሚጠና

“ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው ።አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን?” ዮሐ 3፡10

25
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 3.6: ሳምራዊቷ ሴት

የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ 4፡1 – 26

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ አለቃ ወደ ጌታ በሌሊት በመሔድ በግሉ ከጌታ ጋር
ያሳለፈውን ጊዜና በቆይታውም ያተረፈውን ህይወት ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ አይሁድ
ከሚፀየፏቸው ከሰማሪያ ወገን ከሆነች አንዲት ሴት ጋር ጌታ ኢየሱስ ያደረገውን ቆይታና ከእርሱም ንግግር የተነሳ
በሴቲቱ ህይወት ላይ የተፈጠረውን የሕይወት ለውጥ በዝርዝር እናያለን ።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ኢየሱስ በሰማሪያ ማለፍ ለምን ግድ ሆነበት? ወደ ያዕቆብ ጉድጓድስ የሄደበት ምክንያት ምን


ይመስልሀል/ሻል?
2. የሴቲቱ በ6 ሰዓት ወደዚያ ምንጭ የመሄድንና የኢየሱስ ደግሞ በዚያ የመገኘት ምክንያቶች ምን ነበሩ፡፡
3. በቁ. 10 ላይ ኢየሱስ ራሱን “የእግዚያአብሔር ስጦታና” እና “የህይወት ውሃ” ብሎ ይገልጻል፡፡ የዚህን
የህይወት ውሃ ለሴቲቱ ለመስጠት ለምን ፈለገ? ከኢሳያስ 44፡3 ፣ ከኤርምያስ 2፡13 ፣ ራዕይ 21፡6 ፣ ራዕይ
22፡1 እና 17 ጋር በማዛመድ ጥያቄውን መልሱ፡፡
4. ከዚህ ጌታ ከሚሰጠው የህይወት ውሀ መጠጣት የሚችሉ እነማን ናቸው? ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ደግም
ለዘላለም አይጠማም ብሎ በቁጥር 14 ላይ ጌታ የተናገረው ምን ለማለት ፈልጎ ነው?
5. ከቁ. 15 – 19 ጌታ የሴቲቱን ሀጢያት መግለጡ በሴቲቱ ህይወት ላይ ያመጣው ለውጥ ምንድን
ይመስልሃል/ሻል?
6. ከጌታ ጋር ከነበራት ንግግር የተነሳ የሴቲቱ ህይወትና አመለካከት የተለወጠ ይመስልሀል/ሻል ከቁ. 28 – 30
ተመልከቱ፡፡

ከህይወት ጋር ማዛመድ

7. ጌታ የሰማርያቱን ሴት የነፍስ ጥያቄ እንዴት እንደመለሰና ለተጠማው ነፍሷ የህይወት ውሃ ከሆነው ከራሱ
ጋር መገናኘት ብቻ መልስ እንደሆነ የነገራትን ስታዩ ይህንን የእግዚአብሔርን ስጦታ ምን ያህል በግላችሁ
ትፈልጉታላችሁ? ለሌሎችስ ምን ያህል ታካፍሉታላችሁ?

ማጠቃለያ

እኛ ተረዳነውም አልተረዳነውም ነፍሳችን ሁልጊዜ እግዚያብሔርን ትጠማለች፡፡ ለጥማቷም እርካታ ያለው ከአምላኳ
ጋር በመገናኘትና የህይወት ውሀ ምንጭ ከሆነው ከጌታ ከኢየሱስ በመጠጣት ብቻ እንደሆነ በዚህ ክፍል እንረዳለን ፡፡

በቃል የሚጠና

” እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም….” ዮሐ4፡14

26
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 3.7: በምንዝር የተያዘች ሴት

የምንባብ ክፍል፡- ዮሐ 8፡1 – 11

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት አይሁድ ከሚፀየፏቸው ከሰማሪያ ወገን ከሆነች አንዲት ሴት ጋር ጌታ ኢየሱስ ያደረገውን
ቆይታና ከእርሱም ንግግር የተነሳ በሴቲቱ ህይወት ላይ የተፈጠረውን የሕይወት ለውጥ ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው
ጥናታችን ደግሞ ኢየሱስ በደብረ ዘይት ቤተ መቅደስ ሕዝብ ሊያስተምር በነበረበት ማለዳ በዝሙት የተያዘችን ሴት
የኦሪት ህግ መምህራን ወደ ለፍርድ ወደ እርሱ ማቅረባቸውንና ኢየሱስ ግን ሴቲቱን ነጻ ማውጣቱን እናያለን ።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ሴቲቱን በሕዝብ ፊት አቁመው በኃጢአትዋ ጉዳይ ኢየሱስን የጠየቁት ምን ነበር? የጥያቄአቸው ዓላማስ
ምን ነበር?
2. ኢየሱስ ጎንበስ ብሎ በምድር ላይ በጣቱ ጽፎ በጥያቄ ይወተውቱት ለነበሩት ቀና ብሎ የሰጣቸው ምላሽ
ምን ነበር? እነርሱስ ሲሰሙ ከሽማግሌ ጀምሮ አንድ ባንድ የወጡት ምን ስለሆኑ የነበረ ይመስልሃል/ሻል?
3. ብቻውን የቀረው ኢየሱስ በኃጢአት ክስ ከመሃል ቆማ ለነበረችው ሴት ምን አላት? የርሱዋስ ምላሽ ምን
የሚል ነበር?
4. በመጨርሻም ኢየሱስ ለሴቲቱ የሰጣት የተስፋ ቃልና እንዲሁም የማስጠንቀቂያ ምክር ምን የሚል ነው?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

5. ስላልታየብን ብቻ ራስን ንጹሕ አስመስሎ የሰዎች ውድቀት በግልጽ ስለታየ በሌሎች ላይ ለመፍረድ ጣትን
በጭካኔ ከመቀሰር ይልቅ እግዚአብሔር ውስጣችንን በሚያውቅበት ድካማችን ምን ያህል ራሳችንን
መመልከት ይኖርብናል?
6. “ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት ይውገራት” የሚለው የኢየሱስ አነጋገር ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ውጥስ ኃጢአት
ሲፈጸም ወይም ክርስቲያን ነን የሚሉ ወገኖች ላይ የስነ ምግባር ውድቀት ሲከሰት ሳይወገዝ በቸልታ
እንዲታለፍ የሚያበረታታ ነው ለሚሉ ሰዎች ምን ማለት ይቻላል?

ማጠቃለያ

መቼም ሴቲቱ ዝሙት ስትፈጽም የተያዘችው ቢያንስ ከሌላ አንድ ሰው ጋር መሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ ከእናንተ
ኃጢአት የሌለበት በተባሉ ጊዜ የውስጥ ጉዳቸውን ኅሊናቸው መሸከም ስላቃተው አንድ አንድ እያሉ የወጡት እነዚያ
የኦሪት ህግ መምህራን ሴቲቱን ብቻ ማምጣታቸው ስለ ተፈጸመው ኃጢአት ፣ስለ ሙሴ ህግ ተቆርቁረው ወይም
ስለ ሴቲቱ መዳን ገዶአቸው ሳይሆን ሳይሳካ ቀረ እንጂ ኢየሱስን ለማጥመድ ያደርጉት ሙከራ ነበር። ኢየሱስ
የኃጢአተኞች እንጂ የራሱ የኃጢአት ወዳጅ አለመሆኑን በጥብቅ የሚያስተምረን ሴቲቱን “እኔም አልፈረድኩብሽም”
በሰላም ወይም በነጻ ሂጂ ብሎ ከማሰናበቱ በፊት ከእንግዲህ ዳግም ኃጢአት አታድርጊ ብሎ ማስጠንቀቁ
ያስረዳናል።

በቃል የሚጠና

“ኢየሱስም። እኔም አልፈርድብሽም ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት።” ዮሐ 8፡11

27
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ክፍል አራት: ተጣራሽ /Paradoxic/ ከሚመስሉ አስተምህሮቶች ሰባቱ

እርስ በርስ የሚጣረሱ/የሚጋጩ /Paradoxic/የሚመስሉ ሁኔታ ወይም ድርጊት ሀሳብ ገላጭ ዘይቤዎች ሲሆኑ
በባህሪያቸው ተስማምተው ሳሉ በድርጊታቸው ውጤት በጥልቀት ካልተቃኙ የሚታረቁ የማይመስሉ ናቸው። እነዚህ
አገላለጾች በአንድ ላይ ተገናኝተው ሲታዩ የተቃራኒ ነገሮችን አብሮነት የሚያሳዩ ይሆናል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ራሱ ባስተማረበትና ብዙ የእግዚአብሔር እውነቶች የመልዕክት ትርጉም እኛ በለመድነው እና ከአለም በምንሰማው
አቅጣጫ ብቻ የምንረዳው ሳይሆን እግዚአብሔር ሊናገረን ከፈለገው ሀሳብ አንጻር የምንረዳው መንፈሳዊ ምክር
ይሆናል ፡፡ በዚህ ክፍል ሁሉንም ፓራዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮቶች ለመዳሰስ ባንችልም በሚቀጠሉት
ሰባት ጥናቶች የወተሰኑትን ማየታችን እግዚአብሔር ለህይወታችን ያለውን ከማግኘት በተጨማሪ ይህንን
የሚመስሉ ሃሳቦችን ለወደፊት መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስናጠና በተሻለ መልኩ ልንረዳ እንድንችል መነሻ ይሆነናል፡፡
በመሆኑም ለዚህ ክፍል የመረጥናቸው ሰባት ተከታታይ አርዕስቶች የሚተከተሉት ናቸው።

ጥናት 4.1 በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አለመጨነቅ

ጥናት 4.2 ራስን በመካድ ነፍስን ማዳን

ጥናት 4.3 ሞኝነት የሚመስል ጥበብ

ጥናት 4.4 ደካማን ኃያል ሰው የሚያደርግ ጸጋ

ጥናት 4.5 ትህትና የከፍታ ሚስጥር

ጥናት 4.6 ረብ የሆነውን በመጣል ወደ ፊት

ጥናት 4. 7 በመከራ የማነጥፍ ደስታ

እነዚህን የማይታረቁ የሚመስሉትን ሃሳቦች ለማስታረቅ ከመሞከር ባለፈ የእግዚአብሔር ልብ ለእኛ እንዲሆንልን
ወደ እርሱ ቀርበን ከእርሱ መማር እንድንፈቅድ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

28
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 4.1፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አለመጨነቅ

የምንባብ ክፍል ፡-ኢሳ 40፡30–31ና ማቴ 6፡25–33

መግቢያ፡- የክፍል አራት መጀመሪያ በሆነው በዛሬው ጥናታችን በእግዚያአብሔር ላይ ጸንቶ በመቆም እንዴት
መሻገርና ማሸነፍ ሀይልን ማደስ እንደሚቻል እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በኢያሳያስ 40፡ 30 –31 ላይ ሁሉም ይደክማሉ፣ያታክታሉ፣ይወድቃሉ ነገር ግን እግዚአብሄርን


በመተማመን የሚጠባበቁ ግን እንዴት ነው ሃይላቸውን የሚያድሱት?
2. እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ አይታክቱም፣ አይደክሙም እያለ ሲናገር ከንስር ጋር የአማኞችን
ሕይወት ያያያዘው ለምንድነው? ስለ ንስርስ ምን ታውቃለህ (ሽ)? ለቡድኑ አካፍል፡፡
3. በሉቃ 6፡25 –28 ላይ በተደጋጋሚ አትጨነቁ የሚል ቃል አለ፡፡ ጭንቀት ስፍራን እንደሚያስተው ታውቃለህ
(ሽ)?
4. በወጀብና በማዕበል ውስጥ ጸንቶ ለመቆም አማኝ ምን ማድረግ አለበት?
5. ሁሉ እንደሚያስፈልገን የሰማዩ አባታችን እንደሚያውቅ ካወቅን ለምን እንጨነቃለን?

ከሕይወት ጋር ማዛመድ

6. ጌታ “ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚእብሔርን መንግስት ፅድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል


ሲል የሚፈለገውን ትተን የማይፈለገውን እየፈለግን እንደሆነ ትረዳለህ/ትረጃለሽ?
7. ጭንቀትና መከራ፣ ወጀብና ማዕበል የአማኞች በእምነት ጸንቶ መቆም መለኪያ መሣሪያዎች ናቸው ብለህ
ታምናለህ? በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ጸንተህ (ሽ) በመቆም ወደ ተከታዩ ምዕራፍ የተሻገርክብ/የተሻገርሽበት
ጊዜ ነበረ? ከነበረስ ለቡድንህ ማካፍል ትችላለህ፡፡

ማጠቃለያ

የአማኝ ህይወት በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ወደ ዓለም የመጣው የዘለዓለም ህይወት አጀንዳ መኖር ሲሆን ይህ
አጀንዳ ከግብ እንዳይደርስ ብዙ ተግዳሮቶች እንዳሉ እናውቃለን ሆኖም ግን በተግዳሮቶች መሸነፍ ሳይሆን ጸንቶ
በመቆም አደራውን መወጣት ይቻላል፡፡

በቃል የሚጠና

“ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚያብሔርን መንግስት ፅድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨምርላችኋል” ማቴ 6፡33

29
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 4.2: ራስን በመካድ ነፍስን ማዳን

የምንባብ ክፍል ፡ ዮሐ12፡ 20 – 26

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት በእግዚያአብሔር ላይ ጸንቶ በመቆም እንዴት መሻገርና ማሸነፍ ሀይልን ማደስ
እንደሚቻል ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ አንድ አማኝ ነፍሱን ለጌታና ለወንጌል ስራ በዚህ ዓለም
አሳልፎ በመስጠት እንዴት እንደሚያተርፋት እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በዩሐ12፡24 ላይ ጌታ ኢየሱስ “የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልምተች ብቻዋን ትቀራለች ብትምት ግን
ብዙ ታፈራለች” ሊል ስለምንድን ነው የሚናገረው?
2. ነፍሱን በመውደድና በመጥላት እንዴት አንድ ሰው ለዘላለም ሕይወት ነፍሱን ይጠብቃታል?
3. በዩሐንስ 12፡26 ላይ ጌታ ኢየሱስ “የሚያገለግለኝ ይከተለኝ እኔም በምሆንበት ይሆናል አብም
ያከብረቀዋል” ሊል ምን ዓይነት ክብር ነው?
4. በማርቆስ 8፡34 ላይ “በኋላዩ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክም ይከተለኝ” ሲል
ራስን መካድና መስቀል መሸከም እንዴት እናገናኘዋለን?
5. ማርቆስ 8፡38 ላይ በተጠቀስው መሰረት ጌታ ኢየሱስ በእኔ እና በቃሌ የሚያፍር ሲል በጌታና በቃሉ እንዴት
ነው የሚታፈረው? ሮሜ 1፡16 አብራቹህ ተመልከቱ፡፡

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. በዩሐንስ ወንጌልና በማርቆስ ወንጌል እንደተመለክትነው ወይም እንዳነበብነው በእግዚአብሄር መንግስት


አሰራርና በዚህ ዓለም አሰራር መካከል ተቃራኒ አሰራሮች እንዳሉ ይታያል በመሆኑም እንዴት ነው በዚህ
ዓለም ሲስተም ውስጥ ሆነን የእግዚአብሄርን መንግስት አሰራር የምናከናውነው?
7. በማርቆስ ወንጌል 8፡36 ላይ “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል” ይላል
በዚህ ጥቅስ መሰረት በዓለም ሊሰጡህ/ሽ የሚችሉ ነገሮችን ነገር ግን ነፍስህን/ሽን ሊያጎድሉ ሊያከሱ
ብሎም ሊያጨልሙ ወደ ህይወትህ/ሽ የሚመጡበት ጊዜያቶች ነበሩ ከነበሩስ እንዴት
ተወጣሀቸው/ሻቸው? ለቡድንህ አካፍል/ይ፡፡

ማጠቃለያ

የዚህ የምንኖርበት ዓለም መርህ የሚያስተምረን “ከእኔ፣በእኔ፣ለእኔ” ነው በተቃራኒው ግን የእግዚአብሔርን


መንግስት መርህ ደግም ሁሉ በእርሱ ከእርሱ ለእርሱ እንደሆነ መፅሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል በመሆኑም ዛሬ
የምንኖረው ኑሮ በጌታ እንደሆነ በመረዳት መልካሙን ገድል ተጋድለን ማለፍ ይጠበቅብናል፡፡

በቃል የሚጠና

“ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይመቅመዋል” ማርቆስ 8፡36

30
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 4.3 :ሞኝነት የሚመስል ጥበብ

የምንባብ ክፍል ፡1 ቆሮ1፡18 – 31

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት አንድ አማኝ ነፍሱን ለጌታና ለወንጌል ስራ በዚህ ዓለም አሳልፎ በመስጠት እንዴት
እንደሚያተርፋት ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ እግዚአብሔር እንዴት ሞኝ በመሰለ ነገር ጥበበኞችን
እንደጣላቸው፤ እንዳሳፈራቸውና ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔርሞኝነት እንዲጠበብ እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ነው ሲል ምን ማለቱ ነው? ለአኛ ለምንድንስ ኃይሉ እንዴት ነው?
2. የእግዚአብሔር የዚህችን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን ያደረገው እንዴት ነው?
3. አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችንም ጥበብን እንዲሆን ጥበብን ይጥሉ ሲል አይሁድ ምን
ዓይነት ምልክትን ነው የሚለምኑት የግሪክ ሰዎችስ የምን ጥበብ ነው የሚሹት?
4. የእግዚአብሔር ጥበብና የእግዚአብሄር ኃይል ማነው?
5. እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለም ሞኝ ነገር፣ ዳካማ ነገር፣ ምናምንቴ ነገር፣ የተናቀውን ነገር
መረጠ ሲል ጥበበኛና ኃይለ ብርቱ . . . ወዘተ ለእግዚአብሔር አያስፈልጉም ማለት ነው?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. በእግዚአብሔር በስብከት ሞኝነት የማያምኑትን ሊያድን በጎ ፈቃዱ አድርጎ የመረጠበትን ሀሳብ በጥልቀት
ከቡድንህ (ሽ) ጋር ተወያይበት በ1ኛ ቆሮ ምዕ 2፡ 6 – 10 ያለውን ሀሳብ አብረህ (ሽ) ተመለከት (ች)፡፡
7. በህይወትህ አይረባም፣ አይጠቅምም ያልከውን ነገር እግዚአብሔር ለውጦት ለትልቅ እና ለከበረ ነገር
አድርጎት አይተህ (ሽ) ታውቃለህ (ሽ)?

ማጠቃለያ

እግዚአብሔር ለዓለም ሞኝና፣ ደካማ፣ የተናቀ በመሰለ ስራ አንድያ ልጁን ለምት ያውም ለመስቀል ሞት አሳለፎ
በመስጠት እኛን ልጆቹ አደርገን፡፡

በቃል የሚጠና ጥቅስ

“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና፡፡” 1ኛ ቆሮ 1፡18

31
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 4.4 :ደካማን ኃያል ሰው የሚያደርግ ጸጋ

የምንባብ ክፍል፡- 2ኛ ቆሮ 12፡ 1 – 10

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት እግዚአብሔር እንዴት ሞኝ በመሰለ ነገር ጥበበኞችን እንደጣላቸው፤ እንዳሳፈራቸውና
ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔርሞኝነት እንዲጠበብ ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ሐዋርያው ጳውሎስ
ባለፈበት ህይወቱ ጌታን እንዴት እንዳየውና አሁን ደግም ባለበት ሁኔታ ያለበትን የስጋ ድካም በመናገር
የእግዚአብሔር ጸጋ ግን ከድካም እንዴት አበልጦ እንደረዳው ሲያስረዳ እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ከቁ. 1 እስከ 6 ባለውና በተለይም በ ቁ. 1 ጸሀፊው ትምክህት አያስፈልግም ያለው ለምንድን ነው? በዚያ
ፈንታ ምን ተናገረ? ለምን?
2. ጳውሎስ የሥጋ መውጊያ የተሰጠው ለምን እንደሆነ ይናገራል? ይህ መውጊያ ከእርሱ እንዲወሰድ ያደረገው
ነገር ምን ነበር?
3. ይህ መውጊያ በህይወቱ እያለ በኑሮና በአገልግሎቱ በድል በድል (በሃያል) የቻለው እንዴት ነው?
4. ጸጋ ምንድን ነው? የጸጋ ምንጩስ ማነው? ለአገልግሎቱ ምን ያህል ብቃት ሰጠው?
5. በመጨራሻ ከቁ 11 – 13 ጳውሎስ ትምከህቱ ምን እንደሆነ ይናገራል ይሄን በቁ1 ላይ ከተገለጸው ጋር
አወዳድረህ አካፍል፡፡

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. ዛሬ በአንተ ሕይወት መልካም ነው ብለህ የምትመካበት (ጤና፤ዘመድ፤ጓደኛ፤ስራ፤…) ነገር ምን አለ?


7. በህይወት የለኝም በምትለው በድካምህ ወይም ባለብህ ማንኛውም ፈተና የእግዚአብሔር ጸጋ ሃይል ጸጋ
ኃይል እንደሚሆንህ ምን ያህል ተረድተሃል/ ሻል?

ማጠቃለያ

በሕይወታችን ውስጥ የቱንም ያህል የተሳካልን ሰዎች ብንሆን የጎደለ አንድ ነገር አይጠፋም፡፡ ጎድሏል ከምንለው
ነገራችን በላይ ግን የእግዚአብሔርን ጸጋ እንድንሰራ መጠይቅና እርሱን መያዝ የኃይላችን ሚስጥር መሆኑን መረዳት
ያሻናል፡፡ ጸጋውን ደግም በብዙ ለሰጠን መልካም ፍቃድ መሆኑን ተረድተን ሁልጊዜ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት
መቅረብ ይጠበቅብናል፡፡

በቃል የሚጠና

“ጸጋዬ ይበቃሀል፤ ሀይሌ በድካምህ ይፈጸማል፡፡ “2 ቆሮ12፡9

32
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 4.5: ትህትና የከፍታ ሚስጥር

የምንባብ ክፍል፡- ፊል 2፡ 1 – 11

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ሐዋርያው ጳውሎስ ባለፈበት ህይወቱ ጌታን እንዴት እንዳየውና አሁን ደግም ባለበት
ሁኔታ ያለበትን የስጋ ድካም በመናገር የእግዚአብሔር ጸጋ ግን ከድካም እንዴት አበልጦ እንደረዳው ሲያስረዳ
ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ የክርስቶስን ምሳሌነት ሲያሳያቸው እንዴት ሊኖሩ እንደሚገባቸው
የፊልዽስዩስን አማኞች ሲመክር እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቁዎች

1. ሐዋሪያው በቁ. 1 ላይ በህብረታችው መካካል ምን ሊኖር እንዲገባ ይነግራቸዋል? እየንዳንዱን ሀሳብ


አብራርተህ አስረዳ፡፡
2. በቀ. 2 “ሌሎች ከአንተ እንዲሻሉ መቁጠር” እና በዓለም ለሚታየው የራስን ማንነት የማሳውቅ ባህሪ ጋር
ያለውን ልዩነት አስረዳ? በያዕ 4 ቁጥር 1 – 2፣ 5 – 6 ጋር አስተያይተህ አስረዳ፡፡
3. በምዕራፍ 2፡3-4 ላይ የተቀሱትን የኑሮ ዘይቤ ሊኖር የሚችለው ምን ዓይነት ሰው ነው? በ1ኛ ቆሮ 13
ካለው የፍቅር ሃሳብ ጋር አስተያይተህ ሃሳብህን ግለጽ፡፡
4. ከቁ. 6 – 8 ኢየሱስ ማን እንደሆነ ይናገራል? ትህትናን በህይወቱ እንዴት አድርጎ አስተማረን?
5. ከላይ የተገለጹትንም ቁጥሮችና በተለይም ቁ 9 – 11 ባለው ላይ የኢየሱስን ስም እግዚአብሔር ያገነነበት
ምክንያት ምንድን ነው?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. የብርታትና የሀይል ምንጭ ራስን ከፍ በማድረግ ሳይሆን በእግዚአብሔር ፊት ራስህን ዝቅ አድርገህ


በእውነተኛ ትህትና በማገልገል መሆኑ ተረዳህ? ለወደፊትስ በዚህ አንጻር ምን ማድረግ እንዳለብህ ትረዳለህ?
7. የኑሮና የህይወት የትህትና ምሳሌህ ማን እንደሆነ ተማርክ?

ማጠቃለያ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት መኖር እንዳለብን ፍለጋውን ትቶልን የሄደ መሆኑን በመረዳት በነገር ሁሉ
ምሳሌነቱን እግዚእብሔርን ደስ በሚያሰኝ ኑሮ ህይወታችንን እንድንመራ ይጠበቅብናል፡፡

በቃል የሚጠና

“ክርስቶስ ደግም ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና፡፡”1ጴጥ 2፡21

33
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 4.6: ረብ የሆነውን በመጣል ወደ ፊት

የምንባብ ክፍል፡-ፊል3፡4–13

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ሐዋርያው ጳውሎስ የክርስቶስን ምሳሌነት ሲያሳያቸው እንዴት ሊኖሩ እንደሚገባቸው
የፊልዽስዩስን አማኞች ሲመክር ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ይኸው ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ
ክርስቶስ ሲል ለእርሱ ረብ የሆነውን ነገር ሁሉ እንደ ጉድፍ በመቁጠር በሞቱ እንዲመስለው እነደሚመኝ
ለፊልዽስዩስ አማኞች ከእስር ቤት ሆኖ በጻፈው ደብዳቤው የላከላቸውን መልዕክት እናያለን።

የመወያያ ጥያቁዎች

1. ጳውሎስ በስጋ መታመን ካስፈለገ አሉኝ ብሎ የዘረዘራቸው ትምክህቶቹ ምን ምን ናቸው? እዚህን


የጳውሎስ መመኪያዎች በሙሉ ሌሎች ሰዎች በቀላሉ የሚያገኙዋቸው ይመስልሃል/ሻል? ለምን?
2. “ጳውሎስ ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ” ብሎ የሚላቸውን ነገሮች አሁን እንዴት ነው የሚያያቸው? እነዚህን
ነገሮች እንዲንቅ ወይም እንዲጥል ያስቻለምው ምን የሚበልጥ ነገር ተገልጦለት ነው?
3. ጽድቅ የሚገኘው በምን ዓይነት መንገድ እንደሆነ ነው ጳውሎስ የሚናገረው? ከዚህ ጽድቅን ካገኘበት
እምነት የተነሳ ዻውሎስ እንዲያውቅ ወይም ቢሆንለት መምሰል የሚመኘው ጠንካራ መሻት ምንድር ነው?
4. ጳውሎስ አሁን እንዳገኘሁ ወይም ፍጹም እንደሆንሁ አይደለም የሚለው ነገር ምን ይመስልሃል/ ሻል?
ይህንንስ ለማድረግ ምን አደርጋለሁን ይላል?” በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ” በፊቴ ያለውን ለመያዝ
እዘረጋለሁ” ያለውስ ምን ይመስልሃል/ሻል?
5. የሐ. ጳውሎስ በሕይወት የመኖርም ሆነ የመሞት ዋነኛ ግብ ክርስቶስ የነበረ ሲሆን ይህ መሻቱ የተሳካለት
ይመስልሃል /ሻል? ፊል1:23 ና 2ጢሞ4:6-8 በማንበብ ተወያዩበት።

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. ክርስቶስን ዛሬ ምን ያህል የሕይወታችን ዋና ግብ/ትምክህት አድርገነዋል? ከሆነስ ለስጋችን ይጠቅ ሙን


የበሩትን ስለ እርሱ ስንል ንቀን የተውነው ምን አለ? ካልሆነስ ለምን

ማጠቃለያ

የሐ. ጳውሎስ ትልቁ ናፍቆት ከክርስቶስ ጋር እጅግ የቀረበ ግንኙነት በመፍጠር መንገዱን፤ ማንነቱንና ባሕርዩውን
በማወቅ ብቻ ሳይሆን የትንሳኤውን ኃይልም በማወቅ ስለ እርሱ መከራን በመቀበል በሞቱም እንዲመስለው ነበር።
ይህም ግቡ ተሳክቶለታል።እኛም ከዚህ ያነሰ ሕይወት አይጠበቅብንምና ለጊዜው ለስጋችን የሚመቹንን ነገሮች
እንኳን ቢሆን ከነዚህ ሁሉ ስለ ሚበልጠው ጌታ ስንል የሚጠቅሙንን ነገሮች በጸጋው ጉልበት በመናቅ ወደ ግባችን
ልንገሰግስ ይገባናል።

በቃል የሚጠና

“እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ በመከራውም እንድካፈል ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ በሞቱ
እንድመስለው እመኛለሁ።” ፊል 3፡10–11

34
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 4.7: በመከራ የማነጥፍ ደስታ

የምንባብ ክፍል ያዕ 1፡1 – 17ና ፊል4፡ 4 – 6

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ ሲል ለእርሱ ረብ የሆነውን ነገር ሁሉ እንደ ጉድፍ
በመቁጠር በሞቱ እንዲመስለው እነደሚመኝ ለፊልዽስዩስ አማኞች ከእስር ቤት ሆኖ በጻፈው ደብዳቤው
በላከላቸው መልዕክት ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ክርስቲያኖች እንዴት ውጫዊ
ደስታ/Happiness/ ብቻ ሳይሆን በአስቸጋሪና አስከፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እያለፉ እንኳ ቢሆን በመከራ ከሚያጸናው
ጌታ የተነሳ በውስጣዊ ሐሴት(Joy) እንደሚሞሉ በዝርዝር እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በያዕቆብ መልዕክት 1፡2 ላይ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንደሚያደርግላችሁ አውቃችሁ ሲል


እምነት እንዴት ይፈተናል? ከ1ኛ ጴጥሮስ 1፡ 6 – 7 ላይ ከተጻፈው ጋር በማያያዝ መልስ (ሽ)፡፡
2. አንድ ሰው በተለያዩ ፈተናዎች (ችግሮች) ውስጥ እያለፈ እንዴት እንደ ሙሉ ደስታ ሊቆጥረው ይቻላል?
ከሐዋ 5፡41 ጋር በማዛመድ መልስ (ሽ)፡፡
3. በፊል4፡4 ላይ በተጻፈው መሰረት በማን ነው ደስ ሊለን የሚገባው?
4. መከራና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲገጥሙን ከመቆዘምና ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ በደስታ እግዚአብሔር እንደ
አዘጋጅልን መልካም አጋጣሚ በመውሰድ ልንጠቀምበት የምንችለው? የሐዋ16፡ 25 – 34 ያለውን
ተመልከት፡፡

ከህይወት ጋር ማዛመድ

5. የቀድሞ የእምነት አባቶች የደረሰባቸው መከራና ችግር ሳያቆማቸው እንደውም እንደሙሉ ደስታ
በመቁጠር ወንጌልን ለትውልድሁሉ አድርሰዋል ፡፡ ዛሬ እኛ ዘንድ የደረሰውን የወንጌል ተልዕኮ መከራና
ችግርን በመፍራት የገታነው ይመስልሃል (ሻል)?
6. በዕለት ተዕለት ጉዞዋችን መከራን ወይም ችግርን በመፍራት እንደሚገባኝ የወንጌልን ተልዕኮ
አልተወጣሁም ብለህ ታስባለህ (ሽ) የደረሰብህ (ሽ)? መከራስ አለ ወይ? መከራውንስ እንደሙሉ ደስታ
ወሰድከው (ሽው)? ለቡድንህ አካፍል ፡፡

ማጠቃለያ

ዛሬ በዓለማችን ወንጌልን ለማዳረስ ወይም እውነተኛውን የክርስትና ሕይወት ለመኖር በብዙም በጥቂትም ዋጋ
ያስከፍላል ታዲያ ይህንን ስለ ወንጌል የምንከፍለውን ዋጋ እንደሙሉ ደስታ በመቁጠር የተቀበልነውን አደራ
መወጣት የእያንዳንዱ አማኝ ኃላፊነት ስለሆነ ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት ጌታ እንዲረዳን ተግተን መጸለይ
ይጠበቅብናል፡፡

በቃል የሚጠና

“ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜ እላለው ደስ ይበላችሁ፡፡” ፊሊ4፡4

35
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ክፍል አምስት: ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት

ጸሐፊው

የዮሐንስን ራዕይ የጻፈው ሐዋሪያው ዩሐንስ መሆኑን በመጽሀፍ ውስጥ ተጠቅሶ እናገኛለን (1፡4 ፣ 4፣9 ፣ 22፣8)
ከመጽሀፉ እንደምንረዳው ጸሀፊው መጽሀፍትን ጠንቅቆ የሚያውቅ አይሁዳዊ ሰው እና በሰባቱም ትንሹ እስያ
አብያተ ክርስቲያናት የሚታወቅ የቤተክርስቲያን መሪ የነበረ ሰው ነው፡፡ የክርስትና እምነት በጊዜው ከሚሰራው
ከሰይጣን ሀይል በላይና አሸናፊ ወይንም ድል አድራጊ መሆኑን የተገነዘበ ሰው መሆኑን በመጽሀፍ ውስጥ እንረዳለን፡፡

የተጻፈበት ዘመን/የወቅቱ ሁኔታ

ጽሑፉ የተጻፈው ክርስቲያኖች ወደ ስደት እየገቡ በነበረበት ዘመን ነበር፡፡ ሁለቱ የሮም ነገስታቶች ኔሮ(54 – 68
ዓ.ም) እና ዶሚሽን (ዶሚሻን) (81 – 96) ዓ.ም ሲሆን ብዙ የመጽሀፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች መጽሀፉ በእነዚህ ዘመናት
ውስጥ እንደተጻፈ ይስማማሉ፡፡ የሮም መንግስት ነገስቶቻቸው እንዲመለኩ ትዕዛዝ ያወጣበት ጊዜ ስለነበር
ክርስቲያኖች ክርስቶስን እንጂ ቄሳርን አናመልክም በማለት የሚሰደዱበት ዘመን ነበር፡፡ በሰምርኔስ ላለች
ቤተክርስቲያን መከራ መቀበልን እንዳትፈራ (2፡10) በፊላደልፊያም ቤተክርስቲያን ደግም በዓለም ሁሉ ላይ ሲመጣ
ያለው ፈተና መኖሩን (3፡10) ለጌታ የታመነ ምስክር የሆነ አንቲጳስ መገደሉን (2፡13) ምስክርነታቸው
በመጠበቃቸው የተገደሉ ክርስቲያኖች መኖራቸው (6፡9) ዩሐንስም በዚህ ምክንያት በፍጥም ደሴት እስረኛ ሆኖ
መኖሩ ከነበረው መከራ የተነሣ ከክርስቲና አቋማቸውም የተዛነፉ ምዕመናን መኖራቸውንም ጭምር የሚያሳየን
ወቅት ነበር (2፡14 –15፣20) ፡፡

የተጻፈበት ዓላማ

መጽሀፉ የተጻፈው ክርስቲያኖች በእምነታቸው ጸንተው እንዲቆሙ እና ቄሳር አምላክ አለመሆኑን በማወቅ
እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልኩ ለማሳሳብ ነው፡፡ ሰይጣን መከራ ቢያበዛባቸውም እንኳን እስከምት ድረስ
እንዲጸኑ ይመክራቸዋለል፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስ በሚመለስበት ጊዜ ሰይጣንና ተከታዮቹ ወደ ዘላለም ጥፋት ሲሄዱ
ኢየሱስን የሚከተሉ ግን ከኢየሱስ ጋር ወደ ዘላለም ክብር በመግባት ከእርሱ ጋር ይነግሣሉ፡፡በመሆኑም ለዚህ ክፍል
የመረጥናቸው ሰባት ተከታታይ አርዕስቶች የሚተከተሉት ናቸው።

ጥናት 5.1 ኤፌሶን

ጥናት 5.2 ሰምርኔስ


ጥናት 5.3 ጴርጋሞን

ጥናት 5.4 ትያጥሮን

ጥናት 5.5 ሰርዴስ

ጥናት 5.6 ፊላድልፍያ

ጥናት 5.7 ሎዶቅያ

36
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 5.1: ኤፌሶን - የቀድሞውን ፍቅርዋን የተወች ቤተ ክርስቲያን

የምንባብ ክፍል፡ ራዕ 2፡ 1–7

መግቢያ፡-በመጽሐፉ መግቢያ ላይ እንደተመለክትነው የዮሐንስ ራዕይ የተጻፈው በጊዜው መከራ ውስጥ ለነበሩ
ምዕመናን በእምነታቸው እንዲፀኑና እንደያመቻምቹ ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን በኤፌሶን ላለችው ቤተክርስቲያን
የተባለውን መልዕክት እንመለከታለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ለኤፌሶን ቤተክርስተያን መልዕክት የሰጠው ኢየሱስ በምን መልኩ ነው የተገለፀው (ቁ. 1)?
2. የኤፌሶን ቤተክርስትያን የተወደሰችው በምን በምን ነበር? (ቁ.2 - 4 ቁ. 6)
3. የኤፌሶን ቤተክርስትያን የተነቀፈችው በምን ነበር? ቁ. 4
4. የኤፌሶን ቤተ ክርስትያን የተሰጣት ማስጠንቀቂያ ምን ምን ነበር? ቁ 5 – 6
5. ለኤፌሶን ቤተክርስትያን የተሰጠው ተስፋ ምን ነበር? ቁ 7

ከሕይወት ጋር ማዛመድ

6. እንደ ቤተ ክርስቲያን የምንወደስበት እና የምንነቀፍበት ነገር ምን ያለ ይመስልሃል/ሻል ቡድኑ በስፋት


ይወያይበት?
7. እንደ ክርስቲያን በመንፍስ ቅዱስ የምትወቀስበት (ሽበት) በውስጥ የሚሰማህ ነገር ካለ ከቡድኑ ጋር
በመወያያት እርምጃ ውሰድ(ጂ)

ማጠቃለያ

ይህ ክፍል በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በእኛ ሕይወትና አገልግሎት ለተከናወኑ መልካም ክንውኖች እግዚአብሔርን
የምናመሰግንበት ሲሆን ለምንነቀፍበት ነገር ንስሀ እንድንገባና ወደ ብርታት እንድንመለስ ይመክረናል፡፡

በቃል የሚጠና

“እንግዲህ ከወዴት እንደወደቅህ አስብ ንስሃም ግባ የቀደመውንም ስራህን አድርግ” ራዕ 2፡5

37
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 5. 2፡ ሰምርኔስ- ድኻ ደግሞ ሀብታምም ቤተክርስቲያን

የምንባብ ክፍል ፡ ራዕ 2፡8 – 11

መግቢያ፡-ባለፈው ጥናታችን ለኤፌሶን ቤተክርስቲያን የተጻፈውን መልዕክት ቤተክርስቲያኗ የተወደሰችበትንና


የተነቀፈችበትን ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ለሰምርኔስ ቤተ ክርስቲያን የተጻፈውን መልዕክት
እናያለን።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ለስምርኔስ በተጻፈው መልዕክት ኢየሱስ እንዴት ነበር የተገለጸው? ቁ. 8


2. እግዚአብሔር ለስምርኔስ ቤተክርስቲያን “አውቃለሁ” የሚላቸው ነገሮች ምንድን? ናቸው ቁ. 9
3. የሰምርኔስ ቤተክርስቲያን ለሚደርስባት መከራ ምን ዓይነት ምላሽ እንድትሰጥ ያበረታታል? ቁ. 10 – 11

ከሕይወት ጋር ማዛመድ

4. ክርስቲያኖች ያሉበትን ሁኔታ እግዚአብሔር የሚያውቀው መሆኑ ምን ያህል የሚያፅናና መሆኑን


ተነጋገሩበት፡፡
5. የሰምርኔስ ቤተክርስቲያን አለመነቀፏ ለአንተ(ቺ) ምን አስተማረህ?

ማጠቃለያ

እግዚአብሄር ስለስሙ የምናልፍባቸውን ተግዳሮቶችና መከራዎች ያውቃል፤ እንዲሁም የምናልበትን ሀይልና


መንገድ ይሰጠናል

በቃል የሚጠና

“እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የህይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ” ራዕ 2፡11

38
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 5.3: ጴርጋሞን-ትምህርተ ኑፋቄ የሚከተሉትን የሸሸገች ቤተክርስቲያን

የምንባብ ክፍል፡ ራዕ 2፡12 – 17

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ለስምርኔስ ቤተክርስቲያን የተጻፈውን መልዕክት ቤተክርስቲያኒቷ ከፊት ለፊትዋ
ያለውን መከራ ሳትፈራ እስከ ሞት እንኳ በመታመን ለህይወት አክሊል የተዘጋጀች እንድትሆን
የተበረታታችበትን መልዕክት ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው ጥናታችን ደግሞ በጴርጋሞን ላለች ቤተክርስቲያን
የተጻፈውን እናያለን።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በጴርጋሞን ላለች ቤተክርስቲያን በተጻፈው መልክት ኢየሱስ የተገለጠው በምን መልኩ ነበር? ቁ. 12
2. ቤተክርስቲያኒቱ የትና እንዴት እንደነበረች ተገልጻል? ቁ. 13
3. ቤተክርስቲያኒቷ የተወደሰችበት ነጥብ የቱ ነበር? ቁ. 13
4. ቤተክርስቲያኒቱ የታዘዘችውን ትዕዛዝ ካልፈጸመች የሚከተለው ነገር ምን ነበር?
5. ድል ለነሳው የተሰጠ የተስፋ ቃሎች ምንድን ናቸው?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. ከእግዚአብሔር ቃል እውነት ጋር የማይዛመዱትን የስህተት ትምህርቶች ለይተህ ለማወቅና ለመጋፈጥ ያለህ


መንፈሳዊ አቅም ምን እንደሚመስል ተነጋገሩበት፡፡
7. በዛሬ ጊዜ ከእግዚያብሔር ቃል ጋር የሚጣረሱ ትምህርቶች የትኞቹ ናቸው?
8. የእግዚአብሔር መንፈስ ለንስሃ ከጋበዘህ (ሽ) ምን ያህል የተዘጋጀ ልብ እንዳለህ(ሽ) ከቡድናቹህ ጋር
ተነጋገሩበት፡፡

ማጠቃለያ

ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ዘመንና ሁኔታ ውስጥም ብትሆን ፍንተው ያለውን የእግዚአብሄርን የቃሉን እውነት
ማስተማር እንጂ ከሀሰት ትምህርት ጋር ተቻችላ አብራ መኖር የለባትም፡፡

በቃል የሚጠና

“እንግዲህ ንስሃ ግባ አለዚያ ፈጥኜ እመጣለው!” ራዕ 2፡16

39
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 5.4: ትያጥሮን - አሳችዋን ነብይት ችላ ያለች ቤተ ክርስቲያን

የምንባብ ክፍል ራዕ2፡18 – 29

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት በጴርጋምን ላለች ቤተክርስቲያን የተላከውን መልዕክት ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬው
ጥናታችን ደግሞ ከባድ ማስጠንቀቂ የያዘውን የትያጥሮንን ቤተክርስቲያን ማንነትና ባህሪይ እናያለን።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በክፍሉ ክርስቶስ የተገለጠበት መልክ ምን ነበር?


2. የትያጥሮን ቤተክርስቲያን የተነገረላት መልካም ጎን ምንድን ነው?
3. የኤልዛቤል በጎ የሚመስል ሽፋንዋ እና ክፉ ስራዋ እንዴት ተገልጻል? (ተወያዩበት) 20 – 22
4. እግዚአብሄር ለነቢይ ነኝ ባይዋ ኤልዛቤል የሰጠው ከባድ ማስጠንቂያ ምንድን ነው?
5. የትያጥሮን ቤተክርስቲያን የሰራችው ትልቅ ስህተት ምንድን ነው (ከኤልዛቤል ጋር በተያያዘ)? ቁ. 20
6. በትያጥሮን የቀሩ አማኖች የተገለፁበት መንገድና የተሰጣቸው ተስፋ ምንድን ነው? (ቁ 24 - 26)
7. እስከ መጨረሻ ስራውን ለጠበቀ ከክርስቶስ የሚሰጠውን ስጦታ እንዴት ትገልፀዋለህ?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

8. የኤልዛቤል ግልሙትናና ከተሰጣት ማስጠንቀቂያ በአሁን ዘመን ክርስቶስ ሁሉን እንደሚያይ


(እንደሚያውቅ) እና እግዚአብሄር የማያያቸው ለሚመስላቸው ለዛሬዋ ቤተክርስቲያን አገልጋዮችና ለእኛ
ምን ያስተምረናል?

በቃል የሚጠና

“ሥራህን ፍቅርህንም እምነትንም አገልግሎጥንም ትዕግስትንም ከፊተኛው ሥራህ ይልቅ የኋለኛው እንዲበዛ
አውቃለሁ።” ራዕ2፡19

40
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 5. 5: ሰርዴስ- ሙት ቤተክርስቲያን

የምንባብ ክፍል ራዕ 3፡ 1 – 6

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት ለትያጥሮን ቤተክርስቲያን በተጻፈላት መልዕክት ከባድ ማስጠንቀቂያ ተመልክተን ነበር፡፡
በዛሬውጥናታችን ደግሞ የሰርዴስን ቤተከርስቲያን መልዕክት እናያለን።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በሰርዴስ ላለች ቤተክርስቲያን ኢየሱስ በምን መልኩ ነው የተገለጠው?


2. ለቤተክርስቲያኒቱ የተሰጣት ማስጠንቀቂያ ምንድን ነው? ቁ. 2 እና 3
3. የትኛው ስራዋ ነው በአምላክ ፊት ፊጹም ሆኖ ያልተገኘው?
4. በሰርዴስ ያሉ ጥቂት ቅሬታዎችን እንዴት ትገልፃቸዋለህ ዋጋቸውስ ምንድነ ነው? ቀ.4
5. የሰርዴስ ቤተክርስቲያን ያላት ተስፋ ምንድን ነው? ድል ለሚነሳው የተሰጠ የተባረከ ተስፋ ምንድን ነው?
መልዕክቱ ዘመን ተሻጋሪ መሆኑን እንዴት እንረዳለን?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. በቤተክርስቲያኒቱ ከቀሩት (ካሉት) ጥቂት ቅሬታዎች ህይወትና ከታሰበላቸው ዋጋ ምን እንመለከታለን


ወይም የሰርዴስ ቤተክርስቲያን ከእኛ ጋር እንዴት ይዛመዳል?
7. “እኔ እስከመጣ ድረስ” እና “እስከ መጨረሻው” የሚሉ ቃላት ለእኛ ዘመን ቤተክርስቲያን ምን
ያስተምረናል?

ማጠቃለያ

ለዚህች ቤተክርስቲያን የተሰጣትን ከባድ ማስጠንቀቂያ ችላ ሳንል እንደ አማኝ እንደ ህብረትና እንደ ቤተክርስቲያን
መውሰድ የሚገባንን እርምጃ አንድንወስድ መልዕክቱ ያሳስበናል፡፡ የድሉና የአክሊሉ ተካፋዮች እንድነሆን
የሞተብንን ነገር ህያው ማድረግ (ማንሳት) እንጀምር።

በቃል የሚጠና

“ስራህን በአምላኬ ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን ሊሞቱምያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና።” ራዕ3:2

41
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 5.6: ፊላድልፍያ-ታማኝ ቤተክርስቲያን

የምንባብ ክፍል ራዕ 3፡7 – 13

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት በህይወቷ ሙት ከሆነችው እና እውነትን ጠብቀው ራሳቸውን በቅድስና ስላቆዩ ጥቂት
ቅሬታዎች እንዲሁም ከተሰጣት ተስፋ ተመልክተን ነበር፡፡ በዛሬውጥናታችን ደግሞ በታማኝነቷ ከተመሰከረላት ቤተ
ክርስቲያን እንማራለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በዚህ መልዕክት ከሌሎች መልዕክቶች ለየት ባለ መልኩ ክርስቶስ የተገለጠበት ለምንድን ነው?
2. ፊላድልፊያ ቤተክርስቲያና የተወደሰችባቸው ጉዳዮች ምንድን ናቸው?
3. የዳዊት መክፈቻ የሚለው ሀረግ ስለክርስቶስ ምንን ያመለክታል?
4. ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደወደዳት እንዴት ይታወቃል? ቁ. 9
5. ሊመጣ ያለውን የፈተና ስፋትና ጥንካሬ እንዴት ታዩታላችሁ? ሰዓቱስ የትኛው ሰዓት ነው? የተሰጣትስ
ትልቁ ተስፋ ምንድን ነው?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. ከክርስቶስ ስልጣን ምን እንማራለን ለተዘጋብንስ ነገር ምን ተስፋ አለን?


7. እግዚአብሔር የዚህችን ቤተክርስቲያን ምሳሌነት (ነፀብራቅ) በዛሬዋ ቤተክርስቲያን እንዲያመጣ በጋራ
ፀልዩ!!

ማጠቃለያ

ዛሬም የጌታን ቃል በጽናት ጠብቀው ለሚኖሩ ክርስቶስ ከሚመጣው ፈተና ሁሉ መውጫና የተባረከ ተስፍ አለው፡፡

በቃል የሚጠና

“እነሆ በቶሎ እመጣለሁ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ፡፡” ራዕ 3፡11

42
አርዕስታዊ ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /Topical Bible Study Series

ጥናት 5. 7: ሎዶቅያ- ጎስቋለነትዋን ያላወቀች ቤተ ክርስቲያን

የምንባብ ክፍል ፡ራዕ 3፡14-20

መግቢያ፡- ባለፈው ጥናት የፊላድፍያ ቤተ ክርስቲያን የተመሰገነችበትና የተሰጣትን ተስፋ ተመለክተን ነበር፡፡
በዛሬው ጥናታችን ደግሞ የሎዶቂያን ቤተክርስቲያን መልዕክት እናያለን፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ክርስቶስ ለሎዶቂያ ቤተክርስቲያን ራሱን ከገለጠባቸው ባህሪያቱ እና (ታማኝ ፣ እውነተኛ) ለቤተክርስቲያኒቷ


የተፃፈውን መልዕክት እንዴት ታነፃፅራለህ?
2. የሎዶቂያ ቤተክርስቲያን ከሌሎች ለየት ያለ ውድቀቷ ምንድን ነው?
(ያልለየላት). . .መሃል ሰፋሪ. . .የተሰጣት ማስጠንቀቂያስ ምንድን ነው? (ተወያዩበት)
3. ቤተክርስቲያን ትኩስ የምትመስልባቸውን ባህሪያቶቿን እና ቀዝቃዛ የመሰለችበት ማንነቷን ተወያዩባቸው፡፡
4. የተሰጣት የመመለስ ዕድል ምንድን ነው? የክርስቶስ ፍቅር ለዚህች ቤተክርስቲያን እንዴት ተገልፃል? ቀ. 18
እና 19
5. በክፍሉ የቤተክርስቲያኗ ራቁትነት በምን በምን መልኩ ተንፀባረቋል? በቁጥር 20 ላይ የተሰጣት ትልቁ
ተስፋ ምንድን ነው? “ኩል” እንድትኳል የተሰጣትስ ምክር ምንድን ነው?

ከህይወት ጋር ማዛመድ

6. በዚህም ዘመን መሃል ሰፋሪ ፣ ያለየላቸው ሰዎች አሉ ብለህ ታስባለህ? እንዴትና በምን?
7. ከተገለጡ የአንድ ሰው (አካል) በቁሙ የመሞት ምልክቶች ሆነው ከተጠቀሱ 5 (አምስት) ዋና ዋና
መገለጫዎች ምን እንማራለን መፍትሄውስ ዛሬ ምንድን ነው?

ማጠቃለያ

ዛሬም ለሎዶቂያ ቤተክርስቲያን በተሰጣት ማስጠንቀቂያና የተስፋ ቃል (ራዕይ 3፡20) መሰረት ቃሉን ለአላማኞች
መስጠት ትተን በራችንን ብንከፍት ህያው ሊያደርገን እርሱ የታመነ ነው፡፡

በቃል የሚጠና

“እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳለሁ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት
እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።” ራዕ 3፡20

በሰላም አስጀምሮ ያስጨረሰን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን!አሜን!!!

43

Você também pode gostar