0% acharam este documento útil (0 voto)
58 visualizações8 páginas

Metedaderiya Demb

book

Enviado por

migbaru abera
Direitos autorais
© © All Rights Reserved
Levamos muito a sério os direitos de conteúdo. Se você suspeita que este conteúdo é seu, reivindique-o aqui.
Formatos disponíveis
Baixe no formato PDF, TXT ou leia on-line no Scribd
0% acharam este documento útil (0 voto)
58 visualizações8 páginas

Metedaderiya Demb

book

Enviado por

migbaru abera
Direitos autorais
© © All Rights Reserved
Levamos muito a sério os direitos de conteúdo. Se você suspeita que este conteúdo é seu, reivindique-o aqui.
Formatos disponíveis
Baixe no formato PDF, TXT ou leia on-line no Scribd

የ ምግ ባ ሩ ፤ ዳ ን ኤ ል እ ና ጓ ደ ኞ ቻ ቸ ው የ ገ በ ያ ማዕ ከ ል

ግ ን ባ ታ ህ ብ ረ ት ሽ ር ክ ና ማህ በ ር የ መተ ዳ ደ ሪ ያ ደ ን ብ

የ ምግባሩ ፤ ዳንኤል
እና ጓደኞቻቸው የገበያ
ማዕከል ግንባታ ህብረት
ሽርክና ማህበር
የመተዳደሪያ ደንብ

ጥር 09 /2016 ዓ/ም
ወል ዲ ያ , ኢ ት ዮ ጲ ያ
የ ምግ ባ ሩ ፤ ዳ ን ኤ ል እ ና ጓ ደ ኞ ቻ ቸ ው የ ገ በ ያ ማዕ ከ ል
ግ ን ባ ታ ህ ብ ረ ት ሽ ር ክ ና ማህ በ ር የ መተ ዳ ደ ሪ ያ ደ ን ብ

አላማ
1ኛ. የማህበራችን አባልም ይሁን የከተማችን ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት
የቤት ባለቤት ማድረግ እና ቤቶችን እየሰሩ መሸጥ መለወጥ ማከራየት ከመኖሪያ ቤት
በተጨማሪም በሪል እስቴት ልማት ላይ በመሳተፍ የገበያ ማዕከሎችን ሆቴሎችን መገንባት
እና ማከራየት እነድሁም ማስተዳደር የተለያዩ የንግድ ስራዎችን ህጋዊ ፈቃድ በማዉጣት
በንግድ ዘርፍ መሰማራት

2ኛ. እኛ የ ምግባሩ ፤ ዳንኤል እና ጓደኞቻቸው ማህበር አባላት በአንድ ላይ እየኖርን


ማህበራዊ ኑሯችንን እንኖር ዘንድ የጋራ መኖሪያ እና የንግድ ማዕከሎችን በመገንባት ቋሚ
ሃብት ለማፍራት ይህን ማህበር መስርተናል፡፡

ክፍል 1
አንቀፅ 1
አጭር ርዕስ

ይህ ደንብ የ ምግባሩ ፤ ዳንኤል እና ጓደኞቻቸው የገበያ ማዕከል ግንባታ ህብረት ሽርክና


ማህበር የመተዳደሪያ ደንብ ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡

አንቀፅ 2
ትርጓሜ
በዚህ ደንብ ውስጥ የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚሰጠው እስካልሆነ በስተቀር

1. ማህበር ማለት የ ምግባሩ ፤ ዳንኤል እና ጓደኞቻቸው የገበያ ማዕከል ግንባታ


ህብረት ሽርክና ማህበር ማለት ነው፡፡
2. አባል ማለት የ ምግባሩ ፤ ዳንኤል እና ጓደኞቻቸው የገበያ ማዕከል ግንባታ
ህብረት ሽርክና ማህበር አባል የሆነ/ች ማለት ነው፡፡
3. መዋጮ ማለት የማህበሩ አባላት ቅድመ ክፍያ የከፈሉት እና በዬ ወሩ
በተከፈተው አካውንት መሰረት የሚከፈል ወርሃዊ ክፍያ ማለት ነው፡፡

4. ልዩ መዋጮ ማለት በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ወይም በስራ አስፈፃሚወች


የሚወሰን ሆኖ ለማህበሩ አገልግሎት የሚሆን የቦታ የግንባታ ማቴሪያል
የ ምግ ባ ሩ ፤ ዳ ን ኤ ል እ ና ጓ ደ ኞ ቻ ቸ ው የ ገ በ ያ ማዕ ከ ል
ግ ን ባ ታ ህ ብ ረ ት ሽ ር ክ ና ማህ በ ር የ መተ ዳ ደ ሪ ያ ደ ን ብ
መግዥያ ክፍያ ሲያንሳቸው ከመደበኛ ወርሃዊ ክፍያ ዉጭ የሚከፈል ወይም
የሚዋጣ ክፍያ ማለት ነው፡፡

5. ስራ አስፈፃሚ ማለት ከጠቅላላ ማህበሩ አባላት የሚመረጡ ማህበሩን


የሚያንቀሳቅስ ቁጥራቸው ከ3 ያላነሱ ከ7 ያልበለጡ አመራሮች ማለት ነው፡፡
6. እጣ ማለት ማህበሩ ባወጣው ወርሃዊ እና ልዩ መዋጮ መሰረት አሟልቶ የከፈለ
እና ክፍያውን ያላቋረጡ አባል ማንኛውም አባለ እኩል እጣ ያለው ማለት ነው፡፡
7. አበል ማለት የስራ አስፈፃሚወችም ሁኖ ከጠቅላላ አባላቱ በማህበሩ የስራ
እንቅስቃሴ ሲባል የወጡ ወጭወች ማካካሻ ማለት ነው::

አንቀፅ 3
የተፈፃሚነት ወሰን
1. ይህ የመተዳደሪያ ደንብ የሚፀናው ማህበሩ በመንግስት አካላት እዉቅና
ካገኘበት ከ----------- ጀምሮ ለመተዳደሪያ ደንቡ ላይ በሚፈርሙት በሁሉም
የማህበር አባላት ላይ ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡

አንቀፅ 4
የማህበሩ አድራሻ
 የማህበሩ መኖሪያ አድራሻ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ወሎ ዞን
ወልዲያ ከተማ ሲሆን ማህበሩ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችን
በተለያዩ አካባቢወች ሊያስፋፋ ይችላል፡፡

አንቀፅ 5
ዓላማዎች
የ ምግ ባ ሩ ፤ ዳ ን ኤ ል እ ና ጓ ደ ኞ ቻ ቸ ው የ ገ በ ያ ማዕ ከ ል
ግ ን ባ ታ ህ ብ ረ ት ሽ ር ክ ና ማህ በ ር የ መተ ዳ ደ ሪ ያ ደ ን ብ
1. የማህበራችን አባላትንም ሆነ የከተማዉን ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት
የቤት ባለቤት ማድረግ እና ቤቶችን እየሰሩ መሸጥ ማከራዬት እና ማስተዳደር
2. የግለሰቦችን፤ የማህበሮችን እና የተለያዩ ድርጅቶችን በውክልና ማስተዳደር እና
ማከራየት
3. ከመኖሪያ ቤት በተጨማሪ በሪል እስቴት ልማት ላይ መሳተፍ ፤ የገበያ አዳራሾችን
እና ሆቴሎችን መገንባት ማከራየት እና ማስተዳደር
4. በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ መሰማራት
5. ከማህበሩ አላማዎች ጋር ተያያዥ የሆኑ ተግባራትን ማከናወን

አንቀፅ 6
መደበኛ አባላት

 መደበኛ አባላት ማለት መስራች አባላትን እና በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት


በጠቅላላ ጉባዔ ተቀባይነት አግኝተው በአድስ ወዴ ማህበሩ የሚገቡትንም
ይጨምራል፡፡
 አባል ለመሆን ከሚያስፈልጉ መስፈርቶቹ መካከልም፡-
 የማህበሩን አላማ ተገንዝበው ለተፈፃሚነቱ የሚተጋ
 እድሜው በሀገሪቱ ህገ መንግስት ለመደራጀት የደረሰ ማለትም 18 አመት እና
ከዚያ በላይ የሆነ እና ግደታዎችን ለመፈፀም የሚችል
 በጠቅላላ ጉባዔ የሚወሰኑ ተግባሮችን የሚፈፅም እና ለተፈፃሚነታቸው
የበኩሉን ድርሻመወጣት የሚችል ትሩ ስነ ምግባር ያለው
 ማህበሩን በገንዘቡ በጉልበቱ እና በእዉቀቱ ለማጠናከር እንድሁም ወርሃዊ
ክፍያ እና ልዩ መዋጮችን ማህበሩ ባስቀመጠው ጊዜ ገደብ የሚከፍል እና
ለመክፈል አቅም ያለው
 የመደራጀት መብቱ በህግ ያልተገደበ

አንቀፅ 7
የአባላት መብት
የ ምግ ባ ሩ ፤ ዳ ን ኤ ል እ ና ጓ ደ ኞ ቻ ቸ ው የ ገ በ ያ ማዕ ከ ል
ግ ን ባ ታ ህ ብ ረ ት ሽ ር ክ ና ማህ በ ር የ መተ ዳ ደ ሪ ያ ደ ን ብ
በማህበሩ ውስጥ ያሉ ሁሉም አባላት እኩል መብት አላቸው ማለትም የመምረጥ
የመመረጥ ሃሳባቸውን በነፃነት የመግለፅ
 በማህበሩ አባላት ከትርፍ እኩል እንዴ እጣ መጠናቸው የመከፋፈል
 የማህበሩ አባል ሲሞት ችሎታ ሲያጣ ህጋዊ ወራሾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው
በማህበሩ ውስጥ ሊቀጥሉ የመቻል
 የማህበሩ አባላት በራሱ ፈቃድ ወይም በጥፋት ስራ አስፈፃሚው ወይም ጠቅላላ
ጉባዔው ሲወስን መውጣት ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ድርሻው ድርጅቱ
ያለበት እዳ ታስቦ ስራ አስፈፃሚው ሲወስን ይከፈለዋል፡፡ ነገር ግን ለስራ ማስኬጃ
ተብሎ የከፈለው ገንዘብ አይመለስም፡፡
 የማህበሩ አባላት መተዳደሪያ ደንቡን ሳያከብር ቀርቶ ለውሳኔ ከመቅረቡ በፊት
ለስራ አስፈፃሚው ቀርቦ የመደመጥ መብት ይኖረዋል፡፡
 የማህበሩ አላማ እንድሳካ በተናጠል እና በጋራ የመስራት ሀላፊነት አለበት፡፡
 ማህበሩ ችግሮች ሲያጋጥሙት መፍትሄ የማምጣት የማስተካከል እና
ለመፍተሄወቹ መታገል መብት አለው፡፡
 የማህበሩ አባላት እጣውን ለሌላ ወገን በሽያጭ በስጦታ በውርስ የማስተላለፍ
መብት አለው፡፡
 ስራ አስፈፃሚወች ከማህበሩ ልዩ ጥቅም ማግኘት መብት ይኖራቸዋል/ያለ እጣ
የመረጡትን የራሳቸውን ቦታ ሊወስዱ ይችላሉ/ ይህም ከሌሎች ማህበራት ያለ
እና የተወሰዴ ተሞክሮ ጭምር ነው፡፡

አንቀፅ 8
የአባላት ግደታወች
 በማህበሩ አስቸኳይ እና መደበኛ ስብሰባወች ላይ በተጠራበት ቀን እና ሰዓት እና ቦታ
ቀድሞ የመገኘት
 የማህበሩ አላማ የሚያደናቅፉ አስተሳሰቦች እና ተግባሮችን የመታገል
የ ምግ ባ ሩ ፤ ዳ ን ኤ ል እ ና ጓ ደ ኞ ቻ ቸ ው የ ገ በ ያ ማዕ ከ ል
ግ ን ባ ታ ህ ብ ረ ት ሽ ር ክ ና ማህ በ ር የ መተ ዳ ደ ሪ ያ ደ ን ብ
 የማህበሩን ሃብት እና ንብረት የመጠበቅ የመንከባከብ እና የመቆጣጠር
 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴወቹ የሚያስተላልፋቸውን ውሳኔወች አክብሮ የመፈፀም
 የጉባዔ ውሳኔወችን የመተግበር እና ለተግባራዊነታቸው የመትጋት
 የማህበሩ ህገ ደንብ የማክበር እና የማስከብር
 የማህበሩ አባላት እጣ ሽጦ ሲወጣ ለስም ማዞሪያ የተወሰነውን ገንዘብ 10000 /አስር
ሽህ ብር / በቅድሚያ የመክፈል እና ማመልከቻ ቀድሞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ከማህበሩ እውቅና ዉጭ ሽያጭም ሆነ ግዥ መፈፀም በማህበሩ ተቀባይነት
አይኖረውም ፡፡
 ወርሃዊ ክፍያ እና ልዩ ልዩ መዋጮ በመሰብሰቢያ ጊዜ የመክፈል ግደታ አለበት፡፡
ከተወሰነው ጊዜ ገደብ ያሳለፈ ከሆነ ማህበሩ በሚያስቀምጠው መመሪያ መሰረት
ከነቅጣቱ የመክፈል ግደታ ይኖርበታል፡፡
 ወርሃዊ ክፍያ ጊዜው ወር በገባ እስከ 10 ቀን የሚከፈል ሲሆን በዚህ ጊዜ ያልከፈለ
ከሆነ ላሳለፈበት ለ1 ወር ----------- ብር ተቀጥቶ ለሁለት ወር እድል ይሰጠው እና
3ኛው ወር መጨረሻ ላይ ታግዶ በስራአስፈፃሚ ይታያል፡፡ እንዴ አስፈላጊነቱም
ለጠቅላላ ጉባዔው ቀርቦ ውሳኔ ይሰጠዋል፡፡
 ልዩ መዋጮ ከተባለው ጊዜ ያሳለፈ ለ1 ወር -----------ብር ተቀጥቶ ለ1 ጊዜ እድል
እድል ይሰጠውና ለ2ኛ ጊዜ መጨረሻ ከማህበሩ ታግዶ በስራ አስፈፃሚው ውሳኔ
ይሰጠዋል፡፡ እንዴ አስፈላጊነቱ ለጠቅላላ ጉባዔው ሊቀርብ ይችላላ፡፡ ስለዚህ አባላቱ
ከላይ የተዘረዘሩትን ግደታወች ለማክበር እንድሁም ግደታወችን ለመወጣት እና
ለማህበሩ አላማ መሳካት የመታገል ግደታ ይኖርባቸዋል፡፡
 በማህበሩ ፈቃድ እጣውን የሸጠ የማህበር አባል ስም እንዳዛውር 8 ቀን ይሰጠዋል፡፡
ይህን ሳይተገብር የተገኘ ከአባልነቱ ይሰረዛል፡፡
 የማህበሩ እጣ የመሸጫ መነሻ ዋጋ 200000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር / ሲሆን ከዚህ ዋጋ
በታች ሽጦ የተገኘ የማህበሩን ህልውና አደጋ ላይ የጣለ ስለሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ
የሸጠ የማህበሩን መነሻ ዋጋ 50% ይከፍላል፡፡
 የሽያጭ መነሻ ዋጋ በየጊዜው የሚሻሻል ይሆናል፡፡
 እጣዬን ገዥ አጣሁ ካለ ማህበሩ በ50000/ሃምሳ ሽህ ብር / ለማህበሩ መሸጥ
ይችላል፡፡
አንቀፅ 9
የአባላት መዋጮ
የ ምግ ባ ሩ ፤ ዳ ን ኤ ል እ ና ጓ ደ ኞ ቻ ቸ ው የ ገ በ ያ ማዕ ከ ል
ግ ን ባ ታ ህ ብ ረ ት ሽ ር ክ ና ማህ በ ር የ መተ ዳ ደ ሪ ያ ደ ን ብ
 እያንዳንዱ መስራች አባል የስራ ማስኬጃ እና መመዝገቢያ 300ብር መክፈል
ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን ከምስረታው በኋላ የሚገባ በጠቅላላው ጉባዔ የተወሰነውን
25000/ሃያ አምስት ሽህ ብር የሚከፍል ሲሆን ይሄ በየጊዜው በስራ አስፈጻሚ እና
ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ ክፍያው ሊጨምር ይችላል፡፡
 እያንዳንዱ አባል መደበኛ ወርሃዊ ቁጠባ ክፍያ ----------------- ብር በዬ ወሩ
መቆጠብ አለበት፡፡ ነገር ግን ወርሃዊ ክፍያው በዬ አመቱ በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ
ውሳኔ ሊቀያየር ይችላል፡፡
 እነዳስፈላጊነቱ በጠቅላላ ጉባዔ በተወሰነው ውሳኔ መሰረት እና በስራ አስፈፃሚ
ኮሚቴ ሲታመንበት ከመደበኛ ክፍያ በተጨማሪ የተወሰነው ልዩ መዋጮ ብር -----
---------------በዬ ጊዜው ስራ አስፈፃ ሚው በሚሰጠው ዉሳኔ መሰረት ሊጨምር
ይችላል፡፡
 አንድ አባል እጣውን ሽጦ መውጣት ከፈለገ በመጀመሪያ ለስራ አስፈፃሚው በጽሁፍ
ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን ቅድሚያ ለማህበሩ እድል ተሰጥቶት ከጊዜው ሁኔታ
ጋር የተጣጣመ የሽያጭ መጠን ለሻጭ የሚከፈል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ማህበሩ
ካልፈለገው አባሉ ለውጭ ለየመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 አንድ አባል እጣውን ሽጦ ሲወጣ ለስም ማዞሪያ ብር 10000 ብር ለማህበሩ ገቢ
ማድረግ የሚጠበቅበት ሲሆን ይህም ከጊዜው ሁኔታ ጋር እየተገመገመ የሚስተካከል
ይሆናል፡፡

አንቀፅ 10
አባልነት ስለሚቋረጥባቸው መንገዶች

 በጠቅላላ ጉባዔውም ሆነ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውሳኔ መሰረት እያንዳንዱ አባላት ገንዘብ
በዝግ አካውንት ገቢ እንዳደርግ ተነግሮት ፍቃደኛ ካለሆነ ኮሚቴው በአካል አስቀርቦ ችግሩን
አዳመጦ ለውሳኔ ለጠቅላላ ጉባዔ አቅርቦ ውሳኔ ካሰጠበት
 የማህበሩን ጥቅም በሚጎዳ ተግባር የተሰማራ ከሆነ እና የማህበሩን አባላት እና እንድሁም
የማህበሩን በጎ ስም የሚያጠፋ ሃብት እና ንብረትን ከዘረፈ እና በመረጃ ከተደረሰበት/ከተረጋገጠ
/እና ስራ አስፈፃሚው ካመነበት
 የማህበሩን ህግ እና ደንብ አክብሮ የማይንቀሳቀስ ከሆነ
የ ምግ ባ ሩ ፤ ዳ ን ኤ ል እ ና ጓ ደ ኞ ቻ ቸ ው የ ገ በ ያ ማዕ ከ ል
ግ ን ባ ታ ህ ብ ረ ት ሽ ር ክ ና ማህ በ ር የ መተ ዳ ደ ሪ ያ ደ ን ብ
 ወርሃዊም ሆነ ልዩ መዋጮ በተቀመጠው ጊዜ ያልከፈለ ከሆነ
 የመደራጀት መብቱ በህግ የታገዴ የተነፈገ ከሆነ
 ካለ ማህበሩ ወይም ካለ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ ማህበሩን ወክሎ ከሌላ አካል ጋር በማህበሩ
ስም እና ፈቃድ ለራሱ ጥቅም የስራም ሆነ ሌላ ግንኙነት የፈፀመ ከሆነ
 አባሉ የነበረውን እጣ ለሌላ ወገን አሳልፎ የሸጠ ከሆነ
 በህይወት የሌለ ከሆነ ይቋረጣል፡፡

አንቀፅ 11
የጠቅላላ ጉባዔ ስልጣንና ተግባር
የጠቅላላ ጉባዔው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባር ይኖሩታል፡፡

1) ጠቅላላ ጉባዔው የማህበሩ የበላይ አካል ወይም ጠባቂ ነው፡፡


2) የማህበሩን የመተዳደሪያ ደንብ ያፀድቃል አስፈላጊ ሁኖ ሲያገኘው ያሻሽላል፡፡
3) የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴወችን ከጠቅላላ ጉባዔው አባላት ውስጥ ይመርጣል ያፀድቃል፡፡
4) የማህበሩን ቁጥጥር ኮሚቴ ይመርጣል አስፈላጊ ሁኖ ሲያገኘው በሌላ ይቀይራል፡፡
 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ
 “ “ “ ም/ሰብሳቢ
 “ “ “ ፀሃፊ
 “ “ “ ገንዘብ ያዥ
 “ “ “ ሂሳብ ሹም
5) የማህበሩን ንብረት በበላይነት ይቆጣጠራል ለታለመለት አላማ እንድውል ይፈቅዳል ይወስናል፡፡

Você também pode gostar